በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሮማኒያ የኬንያ አምባሳደሯ ባደረጉት የዘረኝነት ንግግር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጠራች


የኬንያ ካርታ
የኬንያ ካርታ

ሮማኒያ፣ 'አፍሪካውያንን ከዝንጀሮዎች ጋር አወዳድረዋል' የሚል ክስ የቀረበባቸውን የኬንያ አምባሳደሯን ድራጎስ ቲጋኡን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጋለች።

ቲጋኡ፣ በሚያዚያ ወር በኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህንፃ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ አንድ ዝንጀሮ በመስኮት ብቅ ሲል፣ "የአፍሪካ ቡድን ከኛ ጋር ተቀላቅሏል" ማለታቸው ነው የተዘገበው።

ሲ ኤን ኤን፣ ከምስራቅ አውሮፓ ልዑካን ጋር ስብሰባውን ያካሂዱ የነበሩ የአፍሪካ ዲፕሎማቶች የሮማኒያውን ዲፕሎማት ንግግር ተቃውመው ማውገዛቸውን የሚያሳይ ዶክመንት ማግኘቱን ዘግቧል። በተጨማሪም ሲ ኤን ኤን፣ ቲጋቡ ለዲፕሎማቶቹ የላኩትን ሁለት የይቅርታ ደብዳቤ መመልከቱንም ገልጿል።

ሮማኒያ በሚያዚያ ወር የተፈፀመውን ክስተት በቅርቡ መረዳቷን አስታውቃለች። የሮማኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁኔታውን አስመልክቶ ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫም "ስለተፈጠረው ነገር በጣም እናዝናለን። በሁኔታው ለተጎዱ ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን" ብሏል።

XS
SM
MD
LG