በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ24 ሰዓታት የተኩስ አቁም ስምምነት ማብቃቱን ተከትሎ በሱዳን ግጭት ቀጥሏል


በሱዳን፣ ካርቱም ሰዎች ንብረቶቻቸውን ይዘው ሲሸሹ፣ ከህንፃዎች በላይ ጭስ ይታያል - ሰኔ 10፣ 2023
በሱዳን፣ ካርቱም ሰዎች ንብረቶቻቸውን ይዘው ሲሸሹ፣ ከህንፃዎች በላይ ጭስ ይታያል - ሰኔ 10፣ 2023

በሱዳን ሁለት ወራትን ባስቆጠረው ጦርነት፣ ለሲቪሎች የተወሰነ እረፍት ሰጥቶ የነበረው የ24-ሰዓት የተኩስ ማቆም ስምምነት ማለቁን ተከትሎ፣ ዛሬ በሱዳን ዋና ከተማ የቦምብ ድብደባ እና ተኩስ መቀጠሉን የዓይን እማኞች አስታወቁ።

ዛሬ ጠዋት ያበቃው የተኩስ ማቆም ስምምነት በተለይ በካርቱም መንቀሳቀስ ሳይችሉ የቆዩ ሲቪሎች ከያሉበት እንዲወጡ እና የሚያስፈልጋቸውን ምግብም ሆነ ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዲሸምቱ አስችሏቸዋል።

ሆኖም ስምምነቱ ካበቃ ከ10 ደቂቃ በኃላ ዋና ከተማው በድጋሚ በግጭት እና በድብደባ መናጥ መቀጠሉን የዓይን እማኞች ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።

በሰሜን ካርቱም እና አጎራባቹ ኦምዱርማን ከተማ ከባድ የመሳሪያ ተኩስ የሚሰማ ሲሆን ከመዲናዋ በስተደቡብ በሚገኘው አል-ሃዋ ጎዳና ላይ ከፍተኛ ውጊያ ተካሂዷል።

የ24-ሰዓቱ የተኩስ ማቆም ስምምነት እሁድ ጠዋት ማብቃቱን ይፋ ያደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ እና የሳዑዲ አረቢያ አሸማጋዮች፣ ስምምነቱ ካልተሳካ የሽምግልና ጥረታቸውን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ አስጠንቅቀው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግብፅ ቅዳሜ እለት ባወጣችው መግለጫ ከዚህ ቀደም ያለ ቪዛ ወደ ሀገሯ መግባት መግባት ይችሉ የነበሩ ሴቶች፣ ከአስራ ስድስት አመት በታች ያሉ ህፃናት እና ከ50 አመት በላይ የሆኑ የእድሜ ባለፀጎች ላይ የመግቢያ መስፈርቷን እንደምታጠናክር አስታውቃለች። ግብፅ ውሳኔውን ያሳለፈችው "ሀሰተኛ የመግቢያ ቪዛ የሚሰጡ በሱዳን ድምበር ላይ ያሉ ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚያደርጉትን ህገወጥ እንቅስቃሴ" ለማስቆም መሆኑን ገልፃለች።

XS
SM
MD
LG