በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ ውስጥ ህጻናትን በስለት በመውጋት የተጠረጠረው እንዲከሰስ ተወሰነ


በስለት የተወጉ ጉዳተኞችን ለማሰብ የመታሰቢያ የአበባ ተቀምጦላቸዋል፡፡
በስለት የተወጉ ጉዳተኞችን ለማሰብ የመታሰቢያ የአበባ ተቀምጦላቸዋል፡፡

የፈረንሳይ ዳኞች በፈረንሳይ አልፕስ ፓርክ ውስጥ ባለፈው ሀሙስ አራት ህጻናትና ሁለት አዋቂዎችን በስለት ወገቶ በመግደል ሙከራ በተጠረጠረው የ31 ዓመት የሶሪያ ስደተኛ ላይ ዛሬ ቅዳሜ የመጀመሪያ ደረጃ ክስ እንዲመሰረት ወሰኑ፡፡

ስሙ ያልተገለጸው ተጠርጣሪ፣ በስዊድን ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እና የሶስት ዓመት ሴት ልጅ ያለችው መሆኑ ተነግሯል፡፡

በተጠቀሰው ፓርክ የመጫወቻ ስፍራ እንዳሉ በስለት የተወጉት ህጻናት እድሜያቸው ከ22 ወራት እስከ 3 ዓመት እንደሚደርስ አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ህጻናቱ በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፣ ሁሉም ለህይወት በሚያሰጋ ሁኔታ ላይ አለመሆናቸው ተመልክቷል፡፡

በፓርኩ መጫወቻ ውስጥ የነበሩት ተጎጂዎቹ ህጻናት ሁለት የፈረንሳይ እና አንድ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው፣ እንዲሁም የ22 ዓመት እድሜ ያላት የሆላንድ ዜጋ መሆናቸውን አቃቢ ህጎቹ አስታውቀዋል፡፡

ተጠርጣሪው አደጋውን ያደረሰበት ምክንያት ለመግለጽም ሆነ ከመርማሪዎቹ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ አለመሆኑ ተዘግቧል፡፡

አቃቢ ህጎች ድርጊቱ ከሽብር ጋር የተያያዘ ጥቃት አይመስልም ያሉ ሲሆን ስለ ተጠርጣሪው የአእምሮ ጤንነት የህክምና መረጃዎችን መጠየቃቸው ተመልክቷል፡፡

በቁጥጥር ስር የሚገኘው ተጠርጣሪ ጥቃቱን ባደረሰበት ወቅት ሴት ልጁን፣ ባለቤቱን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ይጠቅስ እንደነበር በስፍራው የነበሩ የዐይን እማኞችን የጠቀሰው የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጉዳት የደረሰባቸውንና ቤተሰቦቻቸውን መጎብኝታቸው ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG