በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትውልደ ናይጄሪያ አሜሪካዊው የኮሎራዶ ስፕሪንግስ ከተማ ከንቲባ


ትውልደ ናይጄሪያ አሜሪካዊው የኮሎራዶ ስፕሪንግስ ከተማ ከንቲባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:26 0:00

ትውልደ ናይጄሪያ አሜሪካዊው የኮሎራዶ ስፕሪንግስ ከተማ ከንቲባ

ትውልደ ናይጄሪያ አሜሪካዊው ዬሚ ሞቦላዴ፣ የምዕራባዊዋ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛት ኮሎራዶ ስፕሪንግስ ከተማ ከንቲባ ኾነዋል፡፡ በልማዷ ወግ አጥባቂ መሪዎች የሚመረጡባት ኮሎራዶ ስፕሪንግስ፣ የክፍለ ግዛቱ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ናት፡፡

ለከተማዋ ከንቲባነት የተመረጡ የመጀመሪያው ጥቁር ዬሚ ሞቦላዴ፣ ማኅበረሰባዊ ስብጥሯ ከዕለት ወደ ዕለት እየሰፋ ባለችው ከተማ፣ “የሁላችኹም መሪ ሆኜ አገለግላችኋለኹ” ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡ የእርሳቸው መመረጥ፣ “በተለይ ለጥቁር ወጣቶች፣ ከሰማይ በታች የሚሳናቸው እንደሌለ አነቃቂ ተምሳሌትነት እንደሚኖረው”፣እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

የቪኦኤው ሃሩና ሼሁ፣ የተመራጩን ከንቲባ የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት ተከታትሎ ያጠናቀረውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG