በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን የወደመው የኃይል ማመንጫ ግድብ አካባቢውን አጥለቅልቋል


በዩክሬን የወደመው የኃይል ማመንጫ ግድብ አካባቢውን አጥለቅልቋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:06 0:00

በዩክሬን የወደመው የኃይል ማመንጫ ግድብ አካባቢውን አጥለቅልቋል

በደቡብ ዩክሬን የሚገኝ ኖቫ ካኮቭካ የተሰኘ ግድብ እና የኃይል ማመንጫ ጣቢያ መውደሙን ተከትሎ አካባቢው በከፍተኛ ጎርፍ ተጥለቅልቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም የኃይል ማመንጫው ጣቢያ ውድመት የዩክሬንን ህዝብ ችግር የበለጠ የሚያባብስ ነው ብሏል።

አሁን በሩሲያ ቁጥጥር ስር በሚገኘው የዩክሬን ኪርሳን ክልል በሚገኘው ኒፕሮ ወንዝ ላይ የተገነባው ግድብ ማክሰኞ እለት በመፍረሱ የውጊያ ቀጠና የነበረውን አካባቢ አጥለቅልቋል።

ለአደጋው ማን ተጠያቂ እንደሆነ ግን እስካሁን አልታወቀም።

በግድቡ አካባቢ የሚገኙ መንደሮች እና ከተሞች በውሃ መጥለቅለቃቸውን የሚያሳየውን የሳተላይት ምስል ይፋ ያደረገው ማክሳር ቴክኖሎጂ የተሰኘ ኩባንያ ባወጣው መግለጫ 'ኖቫ ካኮቭካ ግድብ እና የኃይል ማመንጫ ተቋሙ በአብዛኛው መውደሙን' አስታውቋል።

ማክሳር ያወጣቸው ምስሎች፣ መኖሪያ ቤቶች እና ህንፃዎች በውሃ ተውጠው ጣሪያቸው ብቻ ከላይ ሆኖ የሚያሳዩ ሲሆን፣ ውሃው ፓርኮችን፣ መንገዶችን እና መሰረተ ልማቶችን አጥለቅልቋል።

አደጋውን ተከትሎ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ምክርቤት ማብራሪያ የሰጡት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ማርቲን ግሪፊትስ፣ የካኮቭካ ግድብ እና ኃይል ማመንጫ ተቋም ውድመት፣ እ.አ.አ በየካቲት 2022 ዓ.ም ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ወዲህ በሲቪል መሰረተ ልማት ላይ የደረሰ ከፍተኛው ጉዳት ነው ብለዋል።

"ዛሬ የሰማነው ዜና የዩክሬን ህዝብ ችግር፣ እስከዛሬ ካየናቸው ሁሉ እየተባባሰ እንደሚሄድ የሚያሳይ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት ጎርፉ ቀለል ሲል እና ሁኔታው ተገምግሞ ምላሾች መሰጠት ሲሲጀምሩ፣ የአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎቶች የበለጠ እንደሚጨምሩ ይጠበቃል።"

በካኮቭካ ግድብ የሚገኘው የውሃ ማጠራቀሚያ በኬርሳን ብቻ ሳይሆን ዛፖሪሺያ እና ኒፕሮ በተባሉት የዩክሬን ከተሞች ለሚኖሩ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የውሃ ምንጭ እና የአካባቢው ህልውና መሰረት ነው።

የዩክሬን ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በኬርሳን አስተዳደር ቢያንስ 40 መንደሮች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በጎርፍ የተጥለቀለቁ ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት ቁጥሩ እየጨመረ እንደሚሄድ ግሪፊትስ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG