በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 በጀት ብር 801.65 ቢሊዮን እንዲኾን አጸደቀ


የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 በጀት ብር 801.65 ቢሊዮን እንዲኾን አጸደቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:31 0:00

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 በጀት ብር 801.65 ቢሊዮን እንዲኾን አጸደቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ የቀጣዩ 2016 ዓ.ም. የመንግሥት በጀት፣ ብር 801 ነጥብ 65 እንዲኾን አጽድቋል፡፡ ምክር ቤቱ፣ ዛሬ በካሔደው ስብሰባ፣ ባጸደቀው የበጀት ረቂቅ፣ የሀገር ደኅንነትን ማስጠበቅ እና በጦርነት የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ማቋቋም፣ ለበጀቱ በታሳቢነት ከተያዙ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል እንደኾኑ፣ በውሳኔው ጠቁሟል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ባለሞያ እና ተንታኝ ዶር. ቆስጠንጢኖስ በርሄ ግን፣ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ካስከተለው ጉዳት በተጨማሪ፣ በአንዳንድ ቦታዎች አሁንም የቀጠሉት ግጭቶች፣ በበጀቱ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚኖራቸው አብራርተዋል፡፡

መንግሥት፥ ከለጋሽ ሀገራት እና ተቋማት፣ የበጀት ድጎማ ለማግኘት፣ እንዲሁም ለመልሶ ማቋቋም እና ግንባታ የሚኾን ድጋፍ ለማግኘት፣ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ አለበት፤ ብለዋል፡፡ በተለይም፣ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋራ በተያያዘ ተጠያቂነትን ከማስፈን፣ እንዲሁም ከብር ምንዛሬ ተመን አኳያ ያሉ ልዩነቶችን መፍታት እንደሚጠበቅበት አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG