በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተኩስ አቁም ፋታ መጠናቀቁን ተከትሎ በካርቱም ግጭት ዳግም ተቀስቅሷል 


የተኩስ አቁም ፋታ መጠናቀቁን ተከትሎ በካርቱም ግጭት ዳግም ተቀስቅሷል
የተኩስ አቁም ፋታ መጠናቀቁን ተከትሎ በካርቱም ግጭት ዳግም ተቀስቅሷል

በሳውዲ አረቢያ እና ዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት በተቀናቃኝ የሱዳን ወታደራዊ አንጃዎች መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ፋታ መጠናቀቁን ተከትሎ እሁድ ዕለት በተለያዩ መዲናዋ አካባቢዎች ግጭት መባባሱን የካርቱም ነዋሪዎች ገለጹ።

የታላቁ መናገሻ ቀጠና የሚባለውን ስፍራ ከመሰረቱት ሶስት ኩታ ገጠም ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው ኡምዱርማን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የጦር ጄቶችን ከሚጠቀመው የሱዳን ጦር እስካሁን ድረስ የተሰጠ መግለጫ የለም ።በአውሮጳዊያኑ ሚያዚያ 15 የገነፈለው የሱዳን ውስጥ ግጭት ከመዲናዋ ውጭ ወዳሉ ስፍራዎች ተስፋፍቶ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ፈጥሯል ።

የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማራዘም የተጀመረው ድርድር ባለፈው ሳምንት ቢቋረጥም ሳዑዲ አረቢያ እና ዩናይትድ ስቴትስ በጄዳ ከሚገኙ የሱዳን ሰራዊት እና የፈጥኖ ደራሹ ኃይል RSF ልዑካን ጋር በየቀኑ መገናኘታቸውን እንደቀጠሉ ተናግረዋል።

"እነዚህ ውይይቶች ያተኮሩት የጄዳ ድርድር ከመቀጠሉ በፊት ሰብዓዊ ዕርዳታን በማመቻቸት እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሁለቱ ወገኖች ሊወስዷቸው በሚገቡ ላይ ዕርምጃዎች ዙሪያ ስምምነት ላይ ለመድረስ ነው" ሲሉ ሁለቱ ሀገራት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ በአውሮፓዊያኑ ግንቦት 22 ተጀምሮ ቅዳሜ አመሻሽ ላይ አብቅቷል። የበረታውን ጦርነት በተወሰነ ደረጃ እንዲቀንስ እና የሰብአዊ አቅርቦት ውስንነት እንዲሻሻል ቢያደርግም እንደ ቀደሙት የዕርቅ ስምምነቶች በተደጋጋሚ ተጥሷል።

ዛሬ እሁድ ጦርነት እንደ ተቀሰቀሰባቸውከተሰማቸው አካባቢዎች መካከል ማዕከላዊ እና ደቡብ ካርቱም እንዲሁም በሰሜን ከጥቁር አባይ ማዶ ባህሪ ይገኙበታል።

XS
SM
MD
LG