የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈ ወርቂ፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሞስኮ መግባታቸውን፣ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል፣ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ፣ ሞስኮ ቫኑኮቫ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩዴንኮ አንዴሬ ተቀብለዋቸዋል፤ ተብሏል።
የልኡካን ቡድናቸውን አስከተለው ሞስኮ የገቡት ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈ ወርቂ፣ በነገው ዕለት፣ የኦፊሴል ስብሰባ እና በአሌክሳንደር የአርበኞች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን እንደሚያስቀምጡ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ በትዊተር ገጻቸው ላይ ካሠፈሩት መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የተመሩ ከፍተኛ ልዑካን በቅርቡ ኤርትራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።