በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኬንያ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ


የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኬንያ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኬንያ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ

ትላንት ሰኞ፣ ድንገት ናይሮቢ የገቡት፣ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፣ ከኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋራ ተወያይተዋል።

ጉብኝቱ የተካሔደው፣ ሞስኮ እና ኪቭ፣ በገቡበት ጦርነት ሳቢያ፣ ከአፍሪካ የሚያገኙትን ድጋፍ ለማጠናከር፣ አንዳቸው የሌላቸውን ዳና እየተከተሉ በሚያካሒዱት ጉብኝት ዲፕሎማሲያዊ ላቂያ ለማግኘት በሚጣጣሩበት ጊዜ ነው፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ተሰሚነት ወዳላት ኬንያ የተደረገው የላቭሮቭ ጉብኝት፣ የዩክሬኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲምትሮ ኩሌባን፣ ያለፈው ሳምንት የናይሮቢ ጉብኝት ተከትሎ የተካሔደ ነው፡፡

በጉብኝታችን ወቅት፥ በንግድ፣ በኢንቨትመንት እና ኢኮኖሚ፣ በባህል እና ሰብአዊ ርዳታ፣ እንዲሁም በትምህርት፣ በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ስለሚኖረን ትብብር እና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ላይ እንነጋራለን፤”

ላቭሮቭ፣ “በጉብኝታችን ወቅት፥ በንግድ፣ በኢንቨትመንት እና ኢኮኖሚ፣ በባህል እና ሰብአዊ ርዳታ፣ እንዲሁም በትምህርት፣ በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ስለሚኖረን ትብብር እና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ላይ እንነጋራለን፤” ሲሉ መናገራቸውን፣ ከጉብኝቱ በፊት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ጉብኝቱ፣ አስቀድሞ ያልተገለጸና ከኬንያ ባለሥልጣናትም በኩል የወጣ መረጃ አልነበረም፡፡

የዓለም ኀያላን ሀገራት፣ 1ነጥብ3 ቢሊዮን ሕዝብ ባላት አፍሪካ ያላቸውን ተጽእኖ ለማሳደግ በሚያደርጉት ፉክክር፣ ላቭሮቭ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ አህጉሪቱን ለበርካታ ጊዜያት ጎብኝተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት፣ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኩሌባ፣ የተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት፣ ከ15 ወራት በላይ በቆየው የዩክሬን ጦርነት የሚያሳዩትን ገለልተኝነት እንዲያቆሙ በመጠየቅ፣ አፍሪካ ከኪቭ ጋራ ያላትን ትስስር እንድታሳድግ ግፊት አድርገዋል፡፡

ሩሲያ ዩክሬንን ለቃ እንድትወጣ፣ ባለፈው የካቲት፣ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የተላለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ ድምፅ ከሰጡ 54 የአፍሪካ አገሮች መካከል 22 የሚኾኑቱ፣ ድምፅ አልሰጡም ወይም ተአቅቦ አድርገዋል፡፡ ውሳኔውን በመቃወም ድምፅ ከሰጡ አገሮች ውስጥ፣ ኤርትራ እና ማሊ ይገኙበታል፡፡

XS
SM
MD
LG