በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተጠለፉት የቺቦክ ልጃገረዶች አሁንም አልተለቀቁም


ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተጠለፉት የቺቦክ ልጃገረዶች አሁንም አልተለቀቁም
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:39 0:00

ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተጠለፉት የቺቦክ ልጃገረዶች አሁንም አልተለቀቁም

የናይጄሪያ የጦር ሠራዊት፣ በአክራሪ እስላማዊው ቡድን ቦኮ ሐራም፣ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የተጠለፉ ሦስት ተጨማሪ ሴት ተማሪዎችን፣ በዚኽ ሳምንት ማስለቀቁ ተዘግቧል፡፡

እ.አ.አ በ2014፣ የቦኮ ሐራም ታጣቂዎች፣ በቦርኖ ክፍለ ሀገር ቺቦክ ከተማ የሚገኝን የመንግሥት ትምህርት ቤት ወርረው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጃገረዶችን ጠልፈው መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡

ከዚያ ወዲህ፣ ከአጋቾቹ ጋራ በተካሔደ ድርድር ብዙዎች ልጃገረዶች ቢለቀቁም፣ አሁንም በጠላፊዎቻቸው እጅ ያሉ ብዙዎች ናቸው፡፡

ቲመቲ ኦቢዙ ከአቡጃ ያጠናቀረውን ዘገባ፣ ቆንጅት ታየ ለአፍሪካ ነክ ርእሶች ፕሮግራም እንደሚከተለው ታቀርበዋለች፡፡

XS
SM
MD
LG