በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የብድር ጣሪያን ለሁለት ዓመት ከፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደረሰ


ሪፐብሊካን የኮንግረስ አባል ኬቨን ማካርቲ
ሪፐብሊካን የኮንግረስ አባል ኬቨን ማካርቲ

ወራትን ከፈጀ ድርድር በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን እና የኮንግረስ አባሉ ረፐብሊካኑ ኬቨን ማካርቲ የፌደራል መንግስቱን የብድር ጣሪያ በጊዜያዊነት ለማሳደግ ተሳማሙ። የሀገሪቱ የብድር ጣሪያ ለሁለት ዓመት ወደ $31.4 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያድግ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ይሄ የአሁኑ ስምምነት የመጨረሻው አይደለም ተብሏል።ይኸም ሀገሪቱ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ያለባትን ብድር ለመክፈል ሳያዳግታት በፊት፣ እቅዱ በኮንግረስ ፊት ለውሳኔ ቀርቦ መጽደቅ ስላለበት ነው።

ኬቨን ማካርቲ ይሄ ስምምነት “ለአሜሪካ ህዝብ የተገባ ነው” ሲሉ ቅዳሜ ዕለት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው አጠር ያለ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

ስምምነቱ ሀገሪቱን የብድር ጣሪያ ለሁለት ዓመታት ያህል ከፍ የሚያደርግ ቢሆንም የገንዘብ አጠቃቀሟ ላይ ግን ገደብ ያበጀ ነው። በተጨማሪም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ማኅበረሰቦች ለመደገፍ ሊሰሩ በሚገቡ ነገሮችን ቅድመ ሁኔታ እና እና መርሃ ግብሮችንም ያካተተ ነው።

ባይደን እና ማካርቲ በስምምነቱ ላይ ለመወያየት ቅዳሜ ዕለት የ90 ደቂቃ የስልክ ንግግር ማድረጋቸው ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG