በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያው ፕሬዘዳንት የምርጫው ውጤት የእኔ ትሩፋት ነው አሉ


የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት መሃማዱ ቡሃሪ
የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት መሃማዱ ቡሃሪ

የናጄሪያው ፕሬዘዳንት መሃማዱ ቡሃሪ አጨቃጫቂ በሆነው የሀገሪቱ የምርጫ ውጤት ላይ ዛሬ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ፕሬዘዳንቱ ለተከታያቸው ስልጣን ከማስረከባቸው በፊት በእሳቸው የስልጣን ዘመን መራጮች ተዓማኒ የሆነ የምርጫ ሂደት እንዲያልፉ ማድረግ መቻሉ የእሳቸው የስልጣን ዘመን ትሩፋት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በምጣኔ ሃብት ዙሪያ ለሚቀርቡባቸው ትችቶች እራሳቸውን ተከላክለዋል።

እ.ኤ.አ በ2015 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ስልጣን የመጡት ቡሃሪ የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት በድጋሚ ለማነቃቃት፣ ሙስናን ለማስቆም እና የደህንነት ዋስትና እንዲሰፍን ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር። ይሁን እንጂ እጅግ ብዙ ናይጄሪያዊያን እነዚህ ነገሮች በእሳቸው የአገዛዝ ዘመን ብሰዋል ይላሉ።

በሌላ በኩል የአዲሱ ስልጣን ተረካቢ ፕሬዘዳንት ቦላ ቲንቡ ሁለት የቅርብ ተቀናቃኞች፤ የምርጫውን ውጤት የተቃወሙ ሲሆን፤ በመጪው ማክሰኞ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው መሰማት ይጀምራል።

ጡረታ የወጡት የቀድሞ ጄነራል እና ፕሬዘዳንት፤ የ80 ዓመቱ ቡሃሪ የየካቲቱ ምርጫ በአፍሪካ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ባላት ሀገር ላይ ዴሞክራሲን ያሳየ ነው ብለዋል። በተጨማሪም የተመረጡትን ፕሬዘዳንት ቲንቡም ከምርጫው ውስጥ ነጥረው የወጡ ምርጡ ተቀናቃኝ ናቸው ሲሉ አድንቀዋል።

XS
SM
MD
LG