ዩናይትድ ስቴትስ አርብ ዕለት በሶማሊያ የአልሻባብ ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት ማድረሷን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጦር ኮማንድ አስታወቀ።
አፍሪኮም ትላንት ቅዳሜ ዕለት “”በአልሻባብ ተዋጊዎች አለ አግባብ የተወሰዱ” ያላቸውን መሳሪያዎች እና የጦር ዕቃዎች ማውደሙን አስታውቋል። ይሁን እንጂ መሳሪያዎቹ እና የጦር መገልገያዎቹ ከየት እንደተሰረቁ ያስታወቀው ነገር የለም።
ጥቃቱ ቡሎ ማረር በተሰኘው አካባቢ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ልዑክ አካባቢ መፈጸሙን አስታውቋል።
ጥቃቱ የተፈጸመውም ‘የሶማሊያ የፌደራል መንግስትን እና የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ልዑክ ለመደገፍ’ መደረጉን አስታውቋል። ጥቃቱን ተከትሎ በተደረገው ዳሰሳ ሲቪሎች ጉዳት እንዳልደረሰባቸው አፍሪኮም ጨምሮ ገልጿል።