በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሴኔጋል በተቃዋሚ ፓርቲ ድጋፊዎች እና በፖሊስ መኻል ግጭት ደረሰ


ፋይል - በሴኔጋል ተቃዋሚዎች ሰልፍ ሲያካሂዱ
ፋይል - በሴኔጋል ተቃዋሚዎች ሰልፍ ሲያካሂዱ

በሴኔጋል፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ኦስማን ሶንኮ ደጋፊዎቻቸውን በጫኑ መኪናዎች ታጅበው በስደቡብ በምትገኘው ኮልዳ ከተማ ሲደርሱ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።


ሶንኮ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል እና በግድያ ማስፈራራት ለቀረበባቸው እና እስከ አስር አመት ሊያሳስራቸው ለሚችለው ክስ በሚቀጥለው ሳምንት ፍርድቤት ለመቅረብ ወደ ሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተጓዙ ባሉበት ወቅት ነው ግጭቱ የተቀሰቀሰው። ሶንኮ የቀረበባቸውን ክስ ይቃወማሉ።

ሶንኮ በቅርቡ በገደብ የተላለፈ የስድስት ወር የእስር ቅጣት ተላልፎባቸው የነበረ ሲሆን ከዚህ በኃላ ፍርድቤት ለሚያቀርብላቸው ጥሪ ምላሽ እደማይሰጡም አስታውቀው ነበር።

ድጋፊዎቻቸው፣ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እና ሶንኮ እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ እንዳይወዳደሩ የቀረበ ክስ ነው ሲሉ የፍርድ ሂደቱን ለመቃወም ሰልፍ ጠርተዋል።

ሶንኮ ከሚኖሩበት፣ ከዳካር በስተደቡብ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ዚንጉዊንኮር ከተማ፣ ወደ ዳካር ያደረጉትን ጉዞ "የነፃነት ጉዞ" ሲሉ በመጥራት ደጋፊዎቻቸው እንዲያጅቧቸው ጥሪ አቅርበዋል። ሆኖም ኮልዳ ላይ ግጭቱ እንዴት ሊቀሰቀስ እንደቻለ እስካሁን በግልፅ አልታወቀም።

XS
SM
MD
LG