በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ጦር የቀድሞ ሰራዊት አባላት እንደገና እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ


በካርቱም ማዕከል በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ በደረሰ ጥቃት ጭስ ሲወጣ ይታያል - ግንቦት 25፣ 2013
በካርቱም ማዕከል በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ በደረሰ ጥቃት ጭስ ሲወጣ ይታያል - ግንቦት 25፣ 2013

የሱዳን ጦር ተጠባባቂዎች እና ጡረታ የወጡ የሰራዊቱ አባላት እንደገና እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀርቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሱዳን ልዩ መልዕክተኛ አድርጎ የሾማቸውን ባለስልጣን እንዲቀይርም ጦሩ ጠይቋል።


ጦሩ፣ የቀድሞ የሰራዊቱ አባላት አቅራቢያቸው ወደሚገኙ የጦር ሰፈሮች በመሄድ እንዲመዘገቡ የጠየቀው፣ ከተቀናቃኙ ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ጋር ለሚያደርገው ውጊያ ሰራዊቱን ለማጠናከር መሆኑ ቢገለፅም፣ ሁኔታው ግጭቱን ሊያባብስ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።


የተኩስ ማቆም ስምምነቱን የሚከታተሉት ሳዑዲ አረብያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ስምምነቱ በተሻለ ሁኔታ እየተፈፀመ ነው ቢሉም፣ ድንገተኛ ውጊያዎች ሳምንቱን ሙሉ ቀጥለዋል። የጦር ሰራዊቱ የሚያካሂዳቸው እንቅስቃሴዎችም ለረጅም ጊዜ ውጊያ እየተዘጋጀ መሆኑን ያመላክታሉ ተብሏል። ጦሩ በቀይ ባህር በኩል ወደ ሱዳን ሊገባ የነበረ ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሱዳን ጦር የተገኘ መረጃም አመልክቷል።


በተያያዘ ዜና የጦሩ ዋና አዛኝ አብደል ፈታህ አልቡርሃን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ አርብ እለት በፃፉት ደብዳቤ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ቮልከር ፐርትስ እንዲነሱ መጠየቃቸው ተገልጿል።

እ.አ.አ በ2021 የተሾሙት ፐርትስ ሱዳን ወደ ሲቪል አገዛዝ እንድትሻገር ግፊት ሳያደርጉ መቆየታቸውን አንዳንድ የጦር ሰራዊቱ አባላት የሚቃወሙ ሲሆን የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሬክ "ዋና ፀሃፊው በደብዳቤው በጣም ደንግጠዋል" ብለዋል። አክለውም "ዋና ፀሃፊው ቮልከር ፐርትስ በሰሩት ስራ በጣም ኩራት ይሰማቸዋል" ያሉት ዱጃሬክ በልዩ ወኪላቸው ያላቸውን ሙሉ እምነትም በድጋሚ እንደሚያረጋግጡ ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG