በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው አአድ የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን አከበረ


የቀድሞው አአድ የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን አከበረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00

የቀድሞው አአድ የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን አከበረ

የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት፣ 60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን፣ በዛሬው ዕለት አክብሮ ውሏል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት፣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር.)፣ አፍሪካ፣ ከጥገኝነት እና ከተለያዩ ችግሮቿ ሳትላቀቅ ነፃ ነች ማለት እንደሚያዳግት ገልጸዋል፡፡

የኅብረቱ የወቅቱ ሊቀ መንበር የኮሞሮሱ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሶማኒ እና የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሐመት ደግሞ፣ የአህጉሪቱን የአንድነት ሕልም ለማሳካት፣ አባል ሀገራት ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር ኄኖክ ጌታቸው፣ ኅብረቱ፥ ባለፉት 60 ዓመታት፣ በራሱ አባል ሀገራት ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘትና በሌሎችም ፈተናዎች ውስጥ ማለፉን ገልጸዋል፡፡

ለቀጣይ የኅብረቱ ርእዮች ስኬት፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ለአህጉሪቱ ውስብስብ ችግሮች፣ በጋራ አቋም ትኩረት መስጠት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG