በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑንትላንድ “ታሪካዊ” የተባለ የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ አካሔደች


ፑንትላንድ “ታሪካዊ” የተባለ የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ አካሔደች
ፑንትላንድ “ታሪካዊ” የተባለ የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ አካሔደች

በሶማልያ ፌዴራላዊ መንግሥት ሰሜናዊ ምሥራቅ ግዛት፣ ራስ ገዝ በኾነችው ፑንትላንድ፣ ከ50 ዓመታት በኋላ በዛሬው ዕለት በተካሔደ የአካባቢ ምርጫ፣ ድምፅ ሰጪዎች ረጅም ሰልፍ ይዘው ተስተውለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትንና የአፍሪካ ኅብረትን ጨምሮ የፑንትላንድ ዓለም አቀፍ አጋሮች፣ ታሪካዊ ብለው የጠሩት የዚኽ የአካባቢ ምርጫ ተጋቦት፣ በተቀረው የሶማልያ ግዛቶች፣ ዴሞክራሲ ዘልቆ እንዲሰማ እና እንዲነቃቃ አስተዋፅኦ ያደርጋል፤ ብለዋል።

ፈላጭ ቆራጭ ናቸው በሚባሉት በዚያድ ባሬ አገዛዝ ወቅት፣ እ.አ.አ በ1969 ከተካሔደው ምርጫ ወዲህ የአሁኑ፣ በአንድ ሰው-አንድ ድምፅ ሥርዐት የተደረገ እንደኾነ ተነግሯል። ራሷን ነፃ አገር አድርጋ በምትቆጥረው በጎረቤት ሶማሊላንድ፣ ተመሳሳይ ምርጫ ቢከናወንም፣ ዓለም እውቅናን ነፍጎታል።

ምርጫው ከተካሔደባቸው ክልሎች መካከል በ33ቱ ውስጥ፣ ባልተገለጸ አንድ የጸጥታ ችግር ምክንያት፣ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዐቱ ወደ ሌላ ጊዜ ተዛውሯል።

“ዛሬ እጅግ ውድ የኾነ ታሪካዊ ቀን ነው፤” ሲሉ፣ የፑንትላንድ የሽግግር ምርጫ ም/ቤት ሊቀ መንበር አብዲሪሳቅ አሕመድ መናገራቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG