በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ለአፍሪካ ቀንድ ቀውስ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ በድርቅ ከተጉዳው ሶማሌ ክልል አዳድሌ ወረዳ ባዮሎው ቀበሌ ነዋሪዋ ወንዝ ወደሚገኝበት አካባቢ ከብቶቿን እየመራች እአአ የካቲት 2/2022
ፎቶ ፋይል፦ በድርቅ ከተጉዳው ሶማሌ ክልል አዳድሌ ወረዳ ባዮሎው ቀበሌ ነዋሪዋ ወንዝ ወደሚገኝበት አካባቢ ከብቶቿን እየመራች እአአ የካቲት 2/2022

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በአፍሪካ ቀንድ ለሚታየው የአየር ንብረት እና የምግብ ቀውስ የሚውል፣ ሰባት ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ፣ ዛሬ በኒው ዮርክ ከተጀመረው የቀንዱ የርዳታ ተስፋ ቃል መግቢያ ኮንፈረንስ ቀደም ብሎ በአወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ረኀብ በቀጣናው ባይታወጅም፣ ዓለም አቀፉ የተራድኦ ድርጅት(IRC) እና ተመድ፤ ርዳታው፥ ኢትዮጵያ፣ በኬንያ እና ሶማልያ በሚሊዮን የሚቆጠሩትንና ችግር ላይ የወደቁትን ሰዎች ሕይወት ሊያድን እንደሚችል አስታውቀዋል።

ተመድ እንደሚለው፣ በአፍሪካ ቀንድ፣ 21 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች የምግብ ርዳታ ያሻቸዋል።

በሶማልያ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ችግር በእጥፍ ማደጉንንና ድርቅ፥ ለአገሪቱ ሕዝብ ሕይወት አስፈላጊ የኾኑትን ከብቶች ማጥፋቱን መግለጫው አመልክቷል።

ዓለም አቀፉ የተራድኦ ድርጅት(IRC) በበኩሉ፣ “ሰው ሠራሽ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በአካባቢው ድርቅን የማስከተል ዕድሉን በ100 እጥፍ ጨምሯል፤” ብሏል።

ሰባት ቢሊዮን ዶላሩ፣ ወደፊት ሊመጡ ያሉትን ቀውሶች በዘመናዊ ሳይንስ ለመቀነስ እና ለመቀልበስ፣ እንዲሁም በቀጣናው ያሉ ሕዝቦች፣ ወደፊት ሊከሠት የሚችልን ድርቅን እንዲቋቋሙ የሚያግዝ ነው፤ ተብሏል።

XS
SM
MD
LG