በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ለዚምባብዌ ሄሊኮፕተሮች ላከች


ፎቶ ዛኑ ፒ ኤፍ ፌስቡክ (ግንቦት 19፣ 2023)
ፎቶ ዛኑ ፒ ኤፍ ፌስቡክ (ግንቦት 19፣ 2023)

በሩሲያ የተሰሩ ሄሊኮፕተሮች ባለፈው ሃሙስ ዚምባብዌ መድረሳቸውንና፣ ይህም ሩሲያ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናቀር የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑ ተዘግቧል።

ሩሲያ ዩክሬን ላይ በፈጸመችው ወረራ ምክንያት ከዓለም መገለል ሲደርስባት፣ ዚምባቡዌ ያንን ባለማድረጓ የሚሰጥ ማበረታቻ ነው ሲሉ ተንታኞች ይናገራሉ።

18 ይሆናሉ የተባሉት ሄሊኮፕተሮች ለሕክምና እና ለድንገተኛ አደጋ የሚውሉ ናቸው ተብሏል።

የዚምባብዌ ፕሬዝደንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ ሄሊኮፕተሮቹ ለአደጋ ግዜ ምላሽ እና ለአገሪቱ የፖሊስ ኃይል አገልግሎት ይውላሉ ብለዋል። ምናንጋዋ አጋጣሚውን በአሜሪካ እና በሌሎችም በአገራቸው ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ለማውገዝ ተጠቅመዋል።

“ቀንበሩ አንገታችን ላይ ከጠለቀ 23 ዓመታት አልፈዋል። በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሊረዱን ከሚፈልጉ አገራት ርዳታቸውን እንቀበላለን፣ የሩሲያ ፌዴሬሽን አንዷ ነች” ብለዋል ምናንጋግዋ።

XS
SM
MD
LG