በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪና ፋሶ እስላማዊ አክራሪዎች ጥቃታቸውን ቀጥለዋል 


ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ወታደሮች በጋና ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ
ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ወታደሮች በጋና ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ

በማዕከላዊ ምሥራቅ ቡርኪና ፋሶ በጂሃዲስቶች የተፈጸመ ነው በተባለ ጥቃት 20 ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

በዚህ ሳምንት ሁለት ግዜ ታጣቂዎች ሁለት መንደሮችን ወረው ሴቶች እና ሕጻናትን ጨምሮ 20 ሰዎችን እንደገደሉ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

አጥቂዎቹ በሁለቱ መንደሮች ቤቶችን ካቃጠሉ በኋላ፣ የቁም ከብቶችን ይዘው ሄደዋል ሲሉ አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ተናግረዋል።

ተጨማሪ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል ፍራቻ ነዋሪዎች መንደሮችን ጥለው እየወጡ እንደሆነ ተነግሯል።

የጸጥታ ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠው፣ አካባቢውን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከጋና እና ኮንጎ በሚዋሰኑት መንደሮች ውስጥ፣ እስልምና አክራሪዎች ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽሙ እንደበር ተነግሯል።

24 ሲቪሎችና 20 የሚሊሺያ አባላት ባለፈው ወር በደረሰ ጥቃት መገደላቸውም ታውቋል።

ከማሊ የሚመጡ ናቸው በሚባሉ የእስልምና ነውጠኞች ላለፉት ስምንት ዓመታት ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት፣ በቡርኪና ፋሶ ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸው ሲነገር፣ ቢያንስ 2 ሚሊዮን የሚሆኑት ተፈናቅለዋል። አንድ ሶስትኛ የሚሆነው የአገሪቱ ክፍል ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ነውም ተብሏል።

XS
SM
MD
LG