በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካሜሩን የኮሌራ ወረርሽን ለመግታት ገበያዎችን ዘጋች


ካሜሩን 2015
ካሜሩን 2015

ካሜሩን፣ በዐሥሩም የአገሪቱ ክልሎቿ በፍጥነት በመዛመት ላይ ያለውን የኮሌራ ውረርሽኝ ለመግታት፣ ገበያዎችን ዘግታለች።

መንግሥት እንዳስታወቀው፣ 20 ሺሕ የሚኾኑ ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተዋል። ከአገሪቱ 26 ሚሊዮን ጠቅላላ ሕዝብ ውስጥ፣ ወደ ሆስፒታል ለሕክምና የሚሔደው ሰው ቁጥር እጅግ አነስተኛ በመኾኑ፣ በበሽታው የታመሙ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር፣ ከተጠቀሰውም ሊበልጥ እንደሚችል ተሰግቷል።

በፍጥነት በመዛመት ላይ የሚገኘውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመግታት፣ በመዲናዋ የሚገኙ ሦስት ዋና ዋና ገበያዎች በባለሥልጣናቱ ተዘግተዋል። በገበያዎቹ በብዛት ከሚውሉት ዕድሜያቸው ከ21 እስከ 35 የሚደርሱ ወንዶች፣ በኮሌራው ከተጠቁት ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ተገልጿል።

ወረርሽኙ መዛመቱ ከታወቀበት ከሚያዝያ 9 ቀን ጀምሮ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ሲታወቅ፣ ሆስፒታሎች በታማሚዎች ተጨናንቀዋል፤ ተብሏል። የሰብአዊ ረድኤት ሠራተኞች፣ ርቀት ባላቸው የገጠር መንደሮች መድረስ ስለማይችሉ፣ የታማሚዎች ቁጥር ከተጠቀሰውም በላይ ሊኾን እንደሚችል፣ የቪኦኤው ሞኪ ኪንዜካ ከያዉንዴ የላከው ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG