በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካርቱም በታጣቂዎች የሚፈጸም ዝርፊያ አሳሳቢ ኾኗል


ሱዳን፤ ግንቦት 2015
ሱዳን፤ ግንቦት 2015

ከሱዳን ሁለት አደገኛ እስር ቤቶች 17ሺሕ ፍርደኞች ሰብረው ወጥተዋል፤

በካርቱም፣ ወደ ሁለተኛ ወሩ የዘለቀው ጦርነት፣ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና በማስከተል ላይ ባለበት ወቅት፣ የታጠቁ ቡድኖች እና ግለሰቦች የሚፈጽሙት ዝርፊያ ሌላ አሳሳቢ ጉዳይ ኾኗል፡፡

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ፣ በየብስ የካርቱም ከተማን በተሻለ እንደተቆጣጠረና ጦር ሠራዊቱ ደግሞ በአየር ድብደባውን እንደቀጠለ ሲነገር፣ ውጊያው ከጀመረበት ከሚያዝያ 7 ቀን ጀምሮ፣ የፖሊስ ኃይሎች በመንገድ ላይ እንደማይታዩ፣ ነዋሪዎች በመናገር ላይ ናቸው።

“ማንም የሚጠብቀን የለም፤ ፖሊስ የለም፤ መንግሥትም የለም። ወንጀለኞቹ ቤታችንን እየሰበሩ ያለንን ሁሉ በመውሰድ ላይ ናቸው፤” ስትል፣ የመንግሥት ሠራተኛ የኾነችው የ35 ዓመቷ ሣራ አብደላዚም ተናግራለች፡፡

17ሺሕ የሚኾኑና በሱዳን ሁለት አደገኛ እስር ቤቶች የነበሩ ፍርደኞች፣ በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ ተለቅቀዋል። ለእስር ቤቱ መሰበር አንዱ ሌላውን ተጠያቂ ያደርጋል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎቹ አባላትም፣ መኪና በመስረቅ እና የሰው ቤትን እንደ ካምፕ በመጠቀም ላይ እንደኾኑ፣ አንዳንድ የዐይን እማኞች ተናግረዋል። የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ግን፣ ይህን የዐይን እማኞቹን ክሥ ያስተባብላል።

XS
SM
MD
LG