በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ 2ሺሕ ጦሯን ማዮት ወደ ተሰኘችው ደሴቷ ላከች


ፍልሰትን ለመቆጣጠር ማዮት ወደ ተባለቸው የፈረንሳይ ደሴት የተላኩ ወታደሮች
ፍልሰትን ለመቆጣጠር ማዮት ወደ ተባለቸው የፈረንሳይ ደሴት የተላኩ ወታደሮች

ከአፍሪካ በስተ ምሥራቅ በኩል በምትገኘውና ማዮት በተሰኘችው የፈረንሳይ ግዛት የሚታየው የፍልሰተኞች ኹኔታ፣ ከቁጥጥር ውጪ ኾኗል፤ በሚል፣ ፈረንሳይ፣ 2ሺሕ የሚኾኑ ወታደሮቿን ወደ ደሴቲቱ ልካለች፡፡

ወታደሮቹ፣ ፍልሰተኞቹን ከግዛቲቱ እንዲያስወጡ፣ መኖሪያቸውን እንዲያፍርሱ እና ሁከት ፈጣሪ ወሮበሎችን እንዲያጠፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።

ዘመቻው፣ ሰብአዊ ሥቅየትን እንዳያስከትል ከወዲሁ ስጋት ሲፈጥር፣ በግዛቲቱ ነዋሪዎች እና ከኮሞሮስ ደሴት በመጡ ፍልሰተኞች መካከል ደግሞ ውጥረት እንዲሰፍን አድርጓል፤ ተብሏል።

የግዛቲቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በተመለከተ፣ እንዲሁም በፈረንሳይ ዜጎች እና በማዮት ነዋሪ ፍልሰተኞች መካከል፣ ባለው የኑሮ ደረጃ ልዩነት ምክንያት የተፈጠረውን ውጥረትም ገሃድ እንዲወጣ አድርጓል።

ማዮት የፈረንሳይ ግዛት አካል ስትኾን፣ በ100 ኪ.ሜ. ላይ የምትገኘው ኮሞሮስ፣ እ.አ.አ በ1975 ዓ.ም. ከፈረንሳይ ነፃነቷን ዐውጃለች፡፡

ማዮት፣ ድህነት የተጫናት የፈረንሳይ አካል ብትኾንም፣ 3ሺሕ 500 ዶላር የደረሰው የነዋሪዎቿ አማካይ ዓመታዊ ገቢ፣ ኮሞሮስ ከሚኖሩት አንጻር ከእጥፍ በላይ ነው።

ይኸው የነፍስ ወከፍ ገቢ እድገት፣ኮሞሮሳውያን ወደ ማዮት ደሴት እንዲያተኩሩ መስሕብ ኾኗል፡፡

XS
SM
MD
LG