በኬንያ 1 ሺሕ ቶን የተበከለ ስኳር ለገበያ እንዲቀርብ አድርገዋል የተባሉ 27 ባለሥልጣናት ለግዜው ከሥራ ታግደዋል።
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ጽ/ቤት ሃላፊ ፌሊክስ ኮስኬ እንዳሉት፣ ስኳሩ ከአምስት ዓመታት በፊት ከውጪ የገባ ሲሆን፣ ቀኑ ያለፈበት በመሆኑ ጥቅም ላይ እንዳይውል እና ለኢንዱስትሪ ነዳጅ ግብአት እንዲውል ትዕዛዝ ተላልፎ ነበር። ለሰው ልጅ ጠቀሜታ እንዳይውል የተባለው ስኳር ባልተለመደ እና ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ለገበያ ቀርቧል ብለዋል ኮስኬ።
የኬንያ ብሔራዊ ደረጃ መዳቢ ባልሥልጣንን ጨምሮ፣ 27 ባለሥልጣናት ለግዜው ከሥራ ታግደዋል። የፖሊስ አባላት እንዲሁም የግብር እና የምግብ ሸቀጥ ባለሥልጣናትም ይገኙበታል ተብሏል።
በኬንያ የስኳር ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር ላይ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በአንድ ሶስተኛ በመጨመር፣ ሁለት ኪሎ የታሸገ ቡና በ 3 ዶላር ወይም 400 ሺሊንግ በመሸጥ ላይ ይገኛል።