በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ እህል ከዩክሬን እንዲጫን ተጨማሪ 60 ቀናትን ፈቀደች


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ኪየቭን በጎበኙበት ወቅት ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ጋር
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ኪየቭን በጎበኙበት ወቅት ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ጋር

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ፣ እህል ከዩክሬን የጥቁር ባሕር ወደቦች ወደ ዓለም ገበያ እንዲጫን የተደረሰውን ስምምነት፣ ሩሲያ፣ ለተጨማሪ 60 ቀናት ማራዘሟን በመልካም ተቀብለዋል።

“የስምምቱ መራዘም ለዓለም መልካም ዜና ነው፤” ብለዋል ጉተሬዥ።

“አንዳንድ ያልተፈቱ ጉዳዮች አሉ፤ ነገር ግን ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ ቱርክ እና ተመድ ምክክራቸውን ይቀጥላሉ፤” ሲሉ ዋና ጸሐፊው አክለዋል።

ለሦስቱ ሀገራት መሪዎች ደብዳቤ መጻፋቸውንና ስምምነቱን በተስፋፋ ኹኔታ ለመቀጠል ተስፋቸውን የገለጹት ጉቴሬዥ፣ ስምምነቱ በዓለም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደኾነ ጠቁመዋል።

ስምምነቱ፣ በዓለም ሰብአዊ ርዳታ በእጅጉ ለሚያሻቸው ሀገራት ምግብ እንዲደርስ አስችሏል፤ ያሉት ጉቴሬዥ፣ በቅርቡ 30 ሺሕ ቶን ስንዴ ወደ ሱዳን መላኩን እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል።

እህል እና ማዳበሪያ፣ ከዩክሬን ተጭኖ እንዲጓጓዝ ለማመቻቸት የተደረሰው ስምምነት በሚገባ አልተተገበረም፤ ስትል፣ ሩሲያ ተደጋጋሚ ወቀሳ ስታቀርብ ትሰማለች፡፡

ካለፈው ነሐሴ ጀምሮ፣ ከዩክሬን ሲወጣ የነበረው እህል፣ ለዓለም ገበያ ወሳኝ የምግብ አቅርቦት ነበር፤ ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይገልጻል።

XS
SM
MD
LG