በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕከላዊ ናይጄሪያ ግጭት የሟቾች ቁጥር 85 ደረሰ


የናይጄሪያ ካርታ
የናይጄሪያ ካርታ

በማዕከላዊ ናይጄሪያ፣ በከብት አርቢዎች እና በገበሬዎች መካከል በተከሠተ ግጭት፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 85 መድረሱን፣ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

በግጭቱ፣ ሦስት ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች መፈናቀላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ለዓመታት፣ ሃይማኖት እና ጎሣ ተኮር ሁከት የማይለየው ሥፍራ እንደኾነ በሚነገርለት ማዕከላዊ ናይጄሪያ፣ ሰኞ ዕለት የጀመረው ግጭት፣ ዐዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ ካሉባቸው በርካታ የጸጥታ ችግሮች አንዱ ነው፤ ተብሏል።

የማዕከላዊ ናይጄሪያ አካባቢ፣ በሰሜን የሚበዛው የእስልምና እምነት ተከታይ ማኅበረሰብ እና በደቡብ ያሉት የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚገናኙበት ቦታ ሲኾን፣ ሰኞ ዕለት ለጀመረው ግጭት፣ የወዲያው መንሥኤው ምን እንደኾነ ማወቅ አልተቻለም።

በሰሜን ምዕራብ እና በማዕከላዊ ናይጄሪያ፣ በተለምዶ የሚካሔደው የበቀል ግድያ ወደ ሰፊ ሁከት ተቀይሮ፣ የታጠቁ ወሮበሎች፥ ለዘረፋ እና ሰዎችን ለማገት ሲሉ፣ መንደሮችን በማጥቃት ላይ ናቸው፤ ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።

720 የሚኾኑ ቤቶች በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን ዘገባው አመልክቷል።

የተጎዱ ሰዎችን ቁጥር በትክክል ማወቅ እንዳልተቻለ፣ ነገር ግን 57 የሚኾኑት በሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ፣ የአገሪቱ የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጿል።

XS
SM
MD
LG