በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የተመድ መልዕክተኛ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ተጠየቀ


ፎቶ ፋይል። በሱዳን ካርቱም ጦርነቱን ተከትሎ ከተማው በጭስ ታፍኖ
ፎቶ ፋይል። በሱዳን ካርቱም ጦርነቱን ተከትሎ ከተማው በጭስ ታፍኖ

በመቶ የሚቆጠሩ የሱዳን ወታደሮች እና ደጋፊዎቻቸው፣ በሱዳን የተመድ ልዩ መልዕክተኛ ቮልከር ፐርዝስ፣ አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ በመጠየቅ፣ በአረፉበት ሆቴል ደጃፍ ላይ ሰልፍ አድርገዋል።

የተለያዩ መለዮችን የለበሱት ሰልፈኞቹ፣ እጃቸውን በማንሣት ቁጣቸውን ሲገልጹ፣ በሁለት መኪኖች ላይ የተጫኑ ወታደሮች ደግሞ ወደ ሰማይ ሲተኩሱ ተስተውለዋል።

በሌላ በኩል፣ በሱዳን የሚካሔደው ውጊያ እየቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ ሁለቱ ተፋላሚ ጀነራሎች፣ በአፍሪካ ኅብረት በኩል ግጭታቸውን እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

በፓን አፍሪካ ፓርላሜንታዊ ጉባኤ ላይ የተናገሩት ሩቶ፣ “ሁለቱ ጀኔራሎች ይህን ረብሕ የሌለው ከንቱ ውጊያቸውን እንዲያቆሙ ልንነግራቸው ይገባል፤” ብለዋል።

በሱዳን የተመድ መልዕክተኛ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:11 0:00

በአገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፋታሕ አል ቡርሃንና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ሠራዊቶች መካከል፣ ከአንድ ወር በላይ ሲካሔድ በሰነበተው ውጊያ፣ አንድ ሺሕ የሚኾኑ ሰዎች እንደሞቱ ሲገመት፣ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቃል አቀባይ የኾኑት ኢዛት ዩሱፍ፣ በሳዑዲ አረቢያ በመካሔድ ላይ ላለው የሰላም ንግግር ቁርጠኛ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋራ የመከሩት ቃል አቀባዩ፣ “በጎረቤት ሀገራት የሚደረገውን ጥረት በመልካም እንቀበላለን፤” ብለዋል። ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ፣“ሲቪሎችን እንደ ከለላ ይጠቀማል፤” የሚለውን ደግሞ ቃል አቀባዩ አስተባብለዋል።

በሱዳን በሚካሔደው ግጭት ምክንያት፣ ችግር ላይ የወደቁ ሰዎችን ለመርዳት፣ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል፤ ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ትላንት ረቡዕ ጥሪ አድርጓል።

XS
SM
MD
LG