በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በቡድን 7 ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጃፓን አቀኑ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

በሄሮሺማ፣ ጃፓን በሚደረገው የቡድን 7 ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዛሬ ረቡዕ ወደዛው አቅንተዋል።

ባይደን ወደ ፓፑዋ ኒው ጊኒ እና አውስትራሊያ የሚያደርጉትን ጉዞ ግን፣ የዕዳ ጣሪያ እና ብድርን በተመለከተ ከአሜሪካ ከኮንግረስ ጋር በሚያደርጉት ድርድር ምክንያት ሰርዘዋል።

እስከ ግንቦት 24 ድረስ ፕሬዝደንቱ እና ኮንግረስ ስምምነት ላይ የማይደርሱ ከኾነ፣ የአሜሪካ መንግሥት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ዕዳውን ሳይከፍል ይቀራል፡፡ ይህም በመላው ዓለም የገንዘብ ቀውስ እንዲከተል ያደርጋል ተብሏል።

“ዕዳችንን በመክፈል በዓለም መድረክ አሜሪካ ያላትን የመሪነት ሃላፊነት እንደምንወጣ እተማመናለሁ። ወደ ዋሽንግተን ተመልሼ ከኮንግረስ ጋር ለመደራደር ስል ወደ ፓፑዋ ኒው ጊኒ እና አውስትራሊያ የማደርገውን ጉዞ ለሌላ ግዜ አስተላልፋለሁ” ሲሉ ባይደን ወደ ጃፓን ከማምራታቸው በፊት ዋሽንግተን ላይ ተናግረዋል።

በአስውትራሊያ፣ ጃፓን፣ አሜሪካ እና ህንድ በመጪው ሳምንት በሲድኒ ሊደረግ የነበረውና ‘የኳድ መሪዎች ጉባኤ’ በመባል የሚታወቀው ስብሰባ እንደማይካሄድ የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንተኒ አልባኒዝ አስታውቀዋል።

“በአሜሪካ የውስጥ ፖለቲካ በዕዳ ጣሪያው ዙሪያ ስምምነት መደረስ፣ ለአገሪቱ ኢኮኖሚምም ሆነ ለዓለም ኢኮኖሚ ወሳኝ በመሆኑ ጎዞውን ለሌላ ግዜ ማስተላላፋቸው ምክንያታዊ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል አንተኒ አልባኒዝ።

ባይደን በጃፓን በኢንዱስትሪ ከበለጸጉ አገራት መሪዎች ጋር ስብሰባ ይቀመጣሉ።

አገራቱ ከቻይና እየመጣ ያለውን የንግድና የመዋዕለ ንዋይ እገዳ እና ማዕቀብ በተመለከተ እንደሚወያዩ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የቡድን 7 አገራት ወደ ቻይና የሚላከውን የውጪ ንግድ እንዲሁም አገራቱ ቻይና ውስጥ የሚያውሉትን መዋዕላ ንዋይ በመቆጣጠርና በማገድ፣ የቻይናን የቴክኖሎጂ ጉዞ እንዲያዘግም ለማደረግና በዓለም ያላትን የአቅርቦት የበላይነት ለመቀነስ ይጥራሉ ተብሏል።

XS
SM
MD
LG