በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እህል ከዩክሬን እንዲወጣ የሚፈቅደው ስምምነት ነገ ያበቃል


ፋይል - በዩክሬን፣ ኢዝማኤል ወደብ፣ ሰራተኞች እህል ሲጭኑ
ፋይል - በዩክሬን፣ ኢዝማኤል ወደብ፣ ሰራተኞች እህል ሲጭኑ

እህል ከዩክሬን ወደ ዓለም ገበያ እንዲለቀቅ ድርድር በማካሄድ ላይ ያሉ ወገኖች በነገው ዕለት የሚያበቃውንና በሩሲያ የተሰጠውን የ60 ቀን ፈቃድ ለማስረዘም ተስፋ ሲያደርጉ፣ ሩሲያ በበኩሏ እህልና ማደበሪያ ከዩክሬን እንዲወጣ ለማመቻቸት የተደረሰው ስምምነት በሚገባ አልተተገበረም ስትል ወቀሳ አቅርባለች፡፡

ባለፈው መጋቢት ሩሲያ እህል ከዩክሬን ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ የ 60 ቀናት ስምምነት ላይ ደርሳ ነበር። ካለፈው ነሐሴ ጀምሮ ከዩክሬን ሲወጣ የነበረው እህል ለዓለም ገበያ ወሳኝ አቅርቦት ነበር ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይገልጻል።

ስምምነቱን ለማራዘም ንግግር በመደረግ ላይ መሆኑን የተመድ ባለሥልጣናት በዚህ ሣምንት ይፋ አድርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በስድስት የአፍሪካ አገራት መሪዎች ይዋቀራል ከተባለው የሰላም ልዑክ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ትናንት አስታውቀዋል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከፑቲን እና ዜሌንስኪ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን እና ከአፍሪካዊው የሰላም ልዑክ ጋር ሞስኮ እና ኪቭ ውስጥ ለመገናኘት መስማማታቸውንም ራማፎሳ ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG