በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕከላዊ ናይጄሪያ ግጭት 30 ሰዎች ተገደሉ


የናይጄሪያ ካርታ
የናይጄሪያ ካርታ

በማዕከላዊ ናይጄሪያ፣ በከብት አርቢዎች እና በገበሬዎች መካከል በተከሠተ ግጭት፣ 30 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ናይጄሪያ አካባቢ፣ በሰሜን የሚበዛው የእስልምና እምነት ተከታይ ማኅበረሰብ እና በደቡብ ያሉት የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚገናኙበት ቦታ ሲኾን፣ ለዓመታት ሃይማኖት እና ጎሣ ተኮር ሁከት የማይለየው ሥፍራ እንደኾነ ተገልጿል።

ከትላንት በስቲያ በተከሠተው ግጭት፣ በከብት ጥበቃ ላይ የነበሩት የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ በአብዛኛው ክርስቲያን ከኾኑት ገበሬዎች ጋራ በአደረጉት የተኩስ ልውውጥ፣ 30 የሚደርሱ ሰዎች እንደተገደሉ፣ አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

በሰሜን ምዕራብ እና በማዕከላዊ ናይጄሪያ፣ በተለምዶ የሚካሄደው የበቀል ግድያ ወደ ሰፊ ሁከት ተቀይሮ፣ የታጠቁ ወሮበሎች፥ ለዘረፋ እና ሰዎችን ለማገት ሲሉ፣ መንደሮችን በማጥቃት ላይ ናቸው፤ ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG