በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተ.መ.ድ. ሱዳናውያንን ለመርዳት 3 ቢሊዮን ዶላር ጠየቀ


በሱዳን ዳርፉር ግዛት የነበረውን ግጭት ሸሽታ በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ የነበረች ልጃገረድ፣ በቻድ ለመጠለል፣ በሱዳን እና ቻድ ድምበር መካከል የሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ አልፋ ስትሄድ
በሱዳን ዳርፉር ግዛት የነበረውን ግጭት ሸሽታ በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ የነበረች ልጃገረድ፣ በቻድ ለመጠለል፣ በሱዳን እና ቻድ ድምበር መካከል የሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ አልፋ ስትሄድ

በሱዳን በሚካሄደው ግጭት ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ ሰዎችን ለመርዳት 3 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ረቡዕ ጥሪ አድርጓል።

2.6 ቢሊዮን ዶላር በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎችን ለመርዳት ያስፈልጋል ያለው በመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ)፣ 25 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ሰብአዊ እርዳታ እና ጥበቃ ይሻሉ ብሏል።

በጄኔቫ የሚገኙት የኦቻ ሃላፊ ራመሽ ራጃሲንጋም እናዳሉት በሱዳን እየተካሄደ ያለው ግጭት ለአገሪቱ ዜጎች እጅግ ከባድ ፈተና ደቅኗል። ሃላፊው ጨምረው በግጭቱ 676 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ትክክለኛ ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ስጋታቸውንም ገልጸዋል።

ግጭቱን ሸሽተው ወደ ጎረቤት አገራት ለተሰደዱት ሱዳናውያን 400 ሚሊዮን ዶላር እንደሚስፈልግ ተገልጿል። እስካሁን 220 ሺሕ ሰዎች ወደ ጉረቤት አገራት እንደሸሹ ሲታወቅ፣ 950 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በአገር ውስጥ ተፈናቅለዋል።

XS
SM
MD
LG