በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ከሱዳን በመግባት ላይ ለሚገኙ ስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ ልታቋቁም ነው


ኢትዮጵያ ከሱዳን በመግባት ላይ ለሚገኙ ስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ ልታቋቁም ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:35 0:00

ኢትዮጵያ ከሱዳን በመግባት ላይ ለሚገኙ ስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ ልታቋቁም ነው

ኢትዮጵያ የሱዳኑን ግጭት ሸሽተው ወደ ግዛቷ በመግባት ላይ ለሚገኙ ስደተኞች፣ የመጠለያ ጣቢያ ለማቋቋም እየሠራች መኾኗን፣ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቀ፡፡

የተቋሙ የኮሙኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ዲሬክተር አቶ በአካል ንጉሤ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ እስከ አሁን ድረስ ከሱዳን ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት ሰዎች መካከል፣ 3ሺሕ200 ጥገኝነት ጠያቂዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡ ለእነኚኽ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ በዐማራ ክልል መተማ አካባቢ፣ የመጠለያ ጣቢያ ለማቋቋም፣ የቦታ ጥናት መደረጉን ዲሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የኮሙኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ዲሬክተር አቶ በአካል ንጉሤ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሱዳኑን ግጭት ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ካሉት ሰዎች መካከል፣ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ሥር ከለላ የሚደረግላቸው ስደተኞች እና ጥገኝት ጠያቂዎች እንደሚገኙባቸው ገልጸዋል፡፡

ለእነዚኽ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ በዐማራ እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች፣ ጊዜያዊ የማቆያ ማዕከላት እንደተገነቡላቸው የተናገሩት አቶ በአካል ንጉሤ፣ በዘላቂነት የሚኖሩባቸውን መጠለያዎች ለማቋቋም አስፈላጊው ሥራ እየተሠራ እንደኾነ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ከሱዳን በመግባት ላይ ለሚገኙ ስደተኞች ድጋፍ በማድረግ ላይ እንዳለች አቶ በአካል ጠቅሰው፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እየቀረበ ያለው እገዛ ግን፣ በቂ እንዳልኾነ አመልክተዋል፡፡

የሱዳኑን ግጭት ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉት ሰዎች ብዛት፣ ከ18 ሺሕ በላይ መድረሱን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ/UN-OCHA/ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG