በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱርኩ ድጋሚ ምርጫ የፖለቲካው ድጋፍ ለፕሬዚዳንት ኤርዶዋን አዘመመ


በቱርኩ ድጋሚ ምርጫ የፖለቲካው ድጋፍ ለፕሬዚዳንት ኤርዶዋን አዘመመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:21 0:00

በቱርኩ ድጋሚ ምርጫ የፖለቲካው ድጋፍ ለፕሬዚዳንት ኤርዶዋን አዘመመ

ቱርክ፣ አሸናፊው ካልተለየበት ያለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ፣ በሚቀጥለው እሑድ፣ ሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማካሔድ ተዘጋጅታለች፡፡ ይኹን እንጂ፣ በመጀመሪያው ዙር የአሸናፊነቱ ድምፅ ለጥቂት ያመለጣቸው የወቅቱ ፕሬዚዳንት ራሲፕ ታይብ ኤርዶዋን፣ አብላጫውን የምክር ቤት መቀመጫ የማግኘት ድጋፍ ያላቸው ይመስላል፡፡

አብላጫውን የምክር ቤት መቀመጫ የሚያስገኝላቸውን የአሸናፊነት ድምፅ ለማግኘት ጥቂት ለጎደላቸው፣ በሥልጣን ላይ ለሚገኙት ፕሬዚዳንት ሬችፕ ታዪፕ ኤርዶዋን ብዙዎቹ ደጋፊዎች፣ በመጪው እሑድ ቀጠሮ የተያዘለት የድጋሚ ምርጫ፣ የደስታቸው ምክንያት ነውና አጥብቀው ይፈልጉታል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ተፎካካሪ ከማል ኪሊችዳሮግል፣ በብዙ የሕዝብ አስተያየት መቀበያዎች መሠረት፥ በአሻቀበው የዋጋ ግሽበት፣ በኑሮ ውድነት ቀውስ እና ለርዕደ መሬቱ ኤርዶዋን አሳይተውታል ከተባለው ግድየለሽነት ጋራ ተዳምሮ፣ ግንባር ቀደም ኾነው በሰፊው እንደሚመሩ ተነግሯቸው ነበር፡፡ በቅድመ ምርጫ ውጤቶቹ ግን፣ በአራት ከመቶ ኤርዶዋን የሚያስከትሏቸው ኾነው ተገኝተዋል፡፡

በአንድ ወቅት፣ የኤርዶዋን ጠንካራ የድጋፍ መሠረት መኾኑ በሚታወቅበት የኢስታንቡል ኡስኩዳር አውራጃ፣ ዛሬ የፕሬዚዳንቱ የምርጫ ተቃዋሚዎች እየተበራከቱ ይታያሉ፡፡ ከማል ኪሊችዳሮግልም፣ በሰፊው የተቀናጀ የምርጫ ዘመቻቸው ዒላማ ከአደረጓቸው ቦታዎች አንዱ ይህ አካባቢ ነበር፡፡ ከመራጮቹ የተገኘው አስተያየት በአንጻሩ ጉራማይሌ ነው፡፡

በመጀመሪያ ስማቸው ብቻ መጠራትን የመረጡት መርቬ፣ ኤርዶዋንን ብቻን የማየት ዝንባሌ አለ፤ይላሉ፡፡ መርቬ አክለውም፣ “ሁልጊዜም ይህን አገር የሚያድኑት እርሳቸው እንደኾኑ ተደርጎ ይታመናል፡፡ እናት አገራቸውን ያድናሉ፡፡ ያ አመክንዮ ሁልጊዜም አለ፡፡ ያን አስተሳሰብ በመጠኑ መስበር እፈልጋለኹ፡፡ አእምሯችንን ክፍት ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ለውጥ ጥሩ ነው፡፡ ሰዎች ግን ያለእርሳቸው መንገድ አይኖርም፤ ድልድይ አይኖርም፤ ዜጎች ይራባሉ፤ ብለው ያምናሉ፤” በማለት ተችተው አማራጩን ያመላክታሉ፡፡

የኡስኩዳር ነዋሪ የኾኑት ኢስማኤል እና ሌሎችም፣ ለምግባቸው ምናልባትም ሌላ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ዓሣ ያጠምዳሉ፡፡ መጨረሻውን ለመወሰን፣ አሁንም ወደ እሑዱ ምርጫ እንደሚያመሩ የተናገሩት ኢስማኤል፣ ይህን አልጠበቅንም፡፡ እውነቱን በግልጽ ለመናገር ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ ነበረን፡፡ ግን ይኸው አሁንም ምንም ለውጥ አልመጣም፡፡ ስለዚህ በጣም ደንግጠናል፡፡ ውጤቱን ማመን አልፈልግም፤ ብለዋል፡፡

ሌላው የኡስኩዳር ነዋሪ የኾኑት የኢስማኤል ጓደኛ ሴም፣ ውጤቱ እንዳልገረማቸው ገልጸው፣ በሁለተኛው ፕሬዚዳንታዊ የማጣሪያ ምርጫ፣ ምን ሊከሠት እንደሚችል መጨነቃቸውን ይናገራሉ፡፡

ሴም፣ ትልቁ ዓሣ ትንሹን ዓሣ እንደገና ውጦታል፡፡ ያን ያህል ቀላል ነው፡፡ ሁለተኛው ዙር የማንወደው ነገር ነው፡፡ ሰዎች ግን ዝግጁ ናቸው፡፡ ለነገሩ ሌላስ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? በማለትም ይጠይቃሉ፡፡

ባለፈው እሑድ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ፣ መራጮች፥ ለምክር ቤት አባላትም ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ የኤርዶዋን ጥምረት፣ የምርክ ቤቱን አብላጫ መቀመጫ እንደሚያገኝ ተንብየዋል፡፡ ይኸውም፣ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ኤርዶዋን እ.ኤ.አ. በመጪው እሑድ፣ ግንቦት 28 ቀን በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ የድጋሚ ምርጫ ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡

የፖለቲካ ተንታኝዋ ሴዘን ኦኔይ፣ ይህንኑ ሲገልጹ፣ “ምክንያቱም ፕሬዚዳንቱ እና ምክር ቤቱ በአንድ አቅጣጫ እንዲሰለፉ እንሻለን፡፡ ያ ርግጥ ነው፤ ለተቃዋሚዎች የግድ ወሳኝ ሲኾን፣ ኤርዶዋንን ለሚወክሉት ደግሞ አዎንታዊ ነገር ነው፤” ብለዋል፡፡

የፖለቲካው ድጋፍ ወደ ኤርዶዋን የሚያዘምም በመሰለበት ወቅት፣ ኪሊችዳሮግል፣ በመጪዎቹ የምርጫ ዘመቻዎች፣ አዳጋች የፖለቲካ አቀበት ይጠበቃቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG