በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታይዋንን ሉአላዊነት "እደፈጥጣለሁ!" ስትል ቻይና ዛተች


የታይዋንን ሉአላዊነት እደፈጥጣለሁ ስትል ቻይና ዛተች
የታይዋንን ሉአላዊነት እደፈጥጣለሁ ስትል ቻይና ዛተች

ማንኛውንም የታይዋን ሉዓላዊነት ለመደፍጠጥ ዝግጁ እንደሆነች ቻይና ዛሬ አስታውቃለች፡፡ ከቻይና ዛቻው የመጣው አሜሪካ ለታይዋን የምታቀርበውን የመከላከያ መሣሪይዎች ሽያጭ በማፋጠን ላይ ባለችበት ወቅት ነው።

በአሜሪካ እና በታይዋን መካከል በቅርቡ እየታየ ያለው ወታደራዊ ግኑኝነት “በጣም ትክክለኛ ያልሆነ እና አደገኛ ሙከራ ነው” ሲሉ የቻይናው መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ታን ኬፊ በለቀቀት የቪዲዮ መልዕክት አስታውቀዋል።

የቻይና ሕዝብ ነጻነት ሠራዊት “ወታደራዊ ስልጠናውን እና ዝግጁነቱን በመቀጠል፣ ማንኛውንም የታይዋንን ሉአላዊነት እንዲሁም ከውጪ የሚመጣን ጣልቃ ገብነት በአስተማማኝ ለመደፍጠጥ ዝግጁ ሲሆን፣ ብሔራዊ ሉአላዊነትን እና ግዛትን በአስተማማኝ ይከላከላል” ብለዋል ቃል አቀባዩ። የውጪ ጣልቃ ገብነት ያሉት፣ አሜሪካንን የሚመለከት ነው ተብሏል።

23 ሚሊዮን ሕዝብ ያላትን ታይዋን፣ ቻይና እንደራሷ ግዛት ነው የምትቆጥረው። አስፈላጊም ከሆነ በኃይል እንደምትቀላቅላት በተደጋጋሚ ዝታለች፡፡

የቻይና የዛሬ ዛቻ፣ አሜሪካ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት መሣሪያ ለታይዋን እንደምትሸጥ እና አንድ መቶ የሚሆኑ ወታደራዊ ባለሙያዎችን ወደ አገሪቱ እንደምትልክ ሪፖርቶች መግለጻቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

XS
SM
MD
LG