በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም የታገሉ ሶማሊያዊ የቴምፕልተን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ


የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም የታገሉት ሶማሊያዊ የቴምፕልተን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም የታገሉት ሶማሊያዊ የቴምፕልተን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም ከፍተኛ ትግል ሲያደርጉ የቆዩት ኤድና አዳን ኢስማኤል የ2023 የቴምፕልተን ሽልማት አሸናፊ ኾነዋል።

እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር 1937 ዓ.ም በእንግሊዝ ቁጥጥር ስር በነበረችው ሶማሊላንድ መዲና ሃርጌሳ የተወለዱት የ85 ዓመቷ ኤድና ኢስማኤል፣ አዋላጅ ነርስ ሲኾኑ፣ ሆስፒታል እና የዩኒቨርስቲ የመሰረቱ የጤና አገልግሎት እንዲዳረሥ የሚታትሩ እንደነበር ሽልማቱ ይፋ በኾኑበት ሥነ ስርዐት ላይ ተገልጿል። ሥራዎቻቸው በሶማሊላንድ የእናቶችን ሞት እንዲቀንስ አድርጓል ተብሏል።

የ2023 የቴምፕልተን ሽልማት አሸናፊ በመኾናቸው 1.4 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ታውቋል። “የሴቶች ግርዛት ከእስልምና አስተምሮት ያፈነገጠ እና ጎጂም ነው " በማለት ልምዱን ለማቋም ሲጎተጉቱ ቆይተዋል፤ ተፅዕኖም አሳድረዋል በሚል ተወድሰዋል።

ኤድና በተጨማሪ በአገራቸው ሶማሊላንድ መኪና ያሽከረከሩ የመጀመሪያው ሴት ሲሆኑ፣ የፖለቲካ ሥልጣንም የጨበጡ የመጀመሪያዋ ሴት ናቸው፡፡

በዓለም የጤና ድርጅትም የሴቶች እና ሕጻናት ጤናን በተመለከተ ሠርተዋል፡፡ ከሽልማቱ የተወሰነውን በአሜሪካ ለሚገኘው ‘ኤድና የማዋለጃ ሆስፒታል’ መሣሪያዎች መግዣ እንዲውል እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG