በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ አገራት ወደ ዩክሬን እና ሩሲያ የሰላም ልዑክ ሊልኩ ነው - ራማፎሳ


የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሶቺ ጥቁር ባህር ሪዞርት በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ላይ (ፋይል)
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሶቺ ጥቁር ባህር ሪዞርት በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ ላይ (ፋይል)

የስድስት አፍሪካ አገራት መሪዎች በቅርቡ ወደ ሩሲያ እና ዩክሬን በመጓዝ በሁለቱ አገራት መካከል የሚካሄደውን አውዳሚ ጦርነት የሚያስቆም መፍትሄ ለመሻት እንደሚጥሩ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ስሪል ራማፎሳ መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌኒስኪ “የሰላም ልዑኩንም ሆነ የአፍሪካ መሪዎቹን በሞስኮ እና ኪቭ ለመቀበል ተስማምተዋል” ሲሉ ራማፎሳ ኬፕ ታውን ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ ኪቭን በድሮንና ሚሳዬል ዛሬ ደብድባለች፡፡ ጥቃቱ በአይነቱ እከአሁን ከተደረጉት በጥንካሬው ለየተ ያለ መሆኑን አንድ የዩክሬን ባለስልጣን አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል በመቶ የሚቆጠሩ ሚሳዬሎችንንና ድሮኖችን ለዩክሬን እንደምትልክ እንግሊዝ ትናንት አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG