በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ 10 አንበሶች በእረኞች ተገደሉ


ፋይል- አምቦሰሊ በተሰኘው የኬንያ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ አንበሳ ምስል
ፋይል- አምቦሰሊ በተሰኘው የኬንያ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኝ አንበሳ ምስል

በኬንያ፣ 10 አንበሶች በእረኞች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ከተገደሉት አንበሶች መካከል ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

አንበሶቹ፣ አምቦሰሊ ከተባለው ብሔራዊ ፓርክ ወጥተው 11 ፍየሎችን በመብላታቸው ምክንያት ነው እረኞቹ በቀስት የገደሏቸው።

መንግሥት እና የእንስሳት ጥበቃ ቡድኖች፣ በአንበሳ ለሚገደሉ የቤት እንስሳት የካሳ ክፍያ ሥርዐት ቢኖራቸውም፣ በአካባቢው በተከሠተው ድርቅ ሳቢያ፣ በርካታ እንስሳትን ያጡት እረኞች፣ የተረፉትን ለመከላከል ማድረግ ያለባቸውን አድርገዋል፤ ሲል አሶሺዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

በፓርኩ ይገኙ ከነበሩ አንበሶች፣ ዕድሜው ረዥም ነው የተባለውና ‘ሉንኪቶ’ የተሰኘው አንበሳ መገደል፣ የእንስሳት መብት ተሟጋች ቡድኖችን አሳዝኗል።

XS
SM
MD
LG