በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀርመን ቢሊየኖች የሚያወጣ አዲስ ወታደራዊ እርዳታ ለዩክሬን ለመስጠት ቃል ገባች


የጀርመን ቻንስለር ኦላ ስኮልዝ፣ ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በርሊን በሚገኘው ፅህፈት ቤታቸው አቀባበል ሲያደርጉላቸው።
የጀርመን ቻንስለር ኦላ ስኮልዝ፣ ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በርሊን በሚገኘው ፅህፈት ቤታቸው አቀባበል ሲያደርጉላቸው።

ጀርመን፣ ኪየቭ የሩሲያን ወረራ ለመከላከል የምታደርገውን ውጊያ ለማገዝ፣ ሶስት ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ አዲስ ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ ይፋ ማድርጓን ተከትሎ፣ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በርሊን ውስጥ ከጀርመን መሪዎች ጋር ስብሰባ አካሂደዋል።

የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሚየርን ለዘለንሲኪ በርሊን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አቀባበር ያደረጉላቸው ሲሆን በሁለቱም ወገን የሚወከሉ አራት አማካሪዎቻቸውን ጨምሮ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል።

የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ስኮልዝም እንዲሁ የሁለትዮሽ ንግግር ከማካሄዳቸው በፊት ለዘለንስኪ በወታደራዊ ክብር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዘለንስኪ አከን ወደታባለች የጀርመን ከተማ በመጓዝ የአውሮፓ ህብረት ለዲሞክራሲ ትልቅ አስተዋዖ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን ሻርላሜይን የተሰኘ የክብር ሽልማት እንደሚቀበሉም ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG