በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱርክ የተጋጋለ ፉክክር የታየበት ምርጫ ተጠናቀቀ


Election officials count ballots at a polling station in Istanbul on May 14, 2023, after polls closed in Turkey's presidential and parliamentary elections.
Election officials count ballots at a polling station in Istanbul on May 14, 2023, after polls closed in Turkey's presidential and parliamentary elections.

ቱርክ ዛሬ እሁድ ፕሬዝዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ ያካሄደች ሲሆን በምርጫው የሚሰጠው ድምፅ በአስርት አመታት ውስጥ ባልታየ ሁኔታ የተጠጋጋ ሊሆን እንደሚችል እና ውጤቱ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃም ተፅእኖ ሊኖረው እንደሚችል ተገምቷል።

የምርጫ ውጤቱ ቱርክን ከ20 አመታት በላይ የመሩትን የፕሬዝዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋንን የፖለቲካ እጣ ፈንታ የሚወስን መሆኑ ተገልጿል። በእሁዱ ምርጫ ከፍተኛ ህዝብ እንደሚሳትፈበት የሚጠበቅ ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ የታየበት ምርጫ ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችልም ተገምቷል።

የዋጋ ግሽበት ከ40 በመቶ በላይ በደረሰበት እና የኑሮ ውድነት ከፍተኛ ችግር በፈጠረባት ቱርክ፣ የኢኮኖሚው ሁኔታ ለአብዛኞቹ መራጮች ዋንኛ ጉዳያቸው ሲሆን፣ አንዳንድ መራጮች ደግሞ ዲሞክራሲን እንደቀዳሚ መስፈርት እንደሚያስቀድሙ ይገልፃሉ።

ኤርዶጋን በመጨረሻው የምርጫ ዘመቻቸው ቀን ባደረጉት ንግግር፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዚህ ምርጫ ከስልጣን ሊያባርሯቸው እንደሆነ በመግለፅ ከሰዋቸዋል። ዋሽንግተን በበኩሏ በምርጫ ወቅት የማንንም ወገን እንደማትደግፍ አስታውቃለች።

ከቅርብ አመታት ወዲህ በቱርክ እና በምዕራቡ አጋሯቿ መካከል የነበረው ግንኙነት፣ አንካራ ከሞስኮ ጋር ያላትን ግንኙነት እያጠበቀች በመሄዷ እና በዲሞክራሲ ዙሪያ ስጋት በመፈጠሩ፣ እየተበላሸ ሄዷል። የኤርዶጋን ተቀናቃኝ የሆኑት ኪሊችዳሮግ በበኩላቸው፣ ቱርክ ከምዕራባዊ አጋሮች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ ቃል ገብተዋል።

XS
SM
MD
LG