በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሳዑዲ አረቢያ የሚካሄደው የሱዳን ድርድር ቀጥሏል


መንገደኞች በጦርነት የምትታመሰውን ሱዳን ሸሽተው፣ በአርግሪን ወደብ በኩል ወደ ግብፅ ሲገቡ - ግንቦት 12፣ 2023
መንገደኞች በጦርነት የምትታመሰውን ሱዳን ሸሽተው፣ በአርግሪን ወደብ በኩል ወደ ግብፅ ሲገቡ - ግንቦት 12፣ 2023
  • በሱዳን ከባድ ውጊያ እንደቀጠለ ነው

የሱዳን ተዋጊዎች ቅዳሜ እለት በካርቱም ጎዳናዎች ላይ ከባድ ውጊያ ማካሄዳቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ። ሁለቱ ወገኖች ዛሬ እሁድ በሳዑዲ አረቢያ የሚያደርጉትን ውይይት በቀጠሉበት ወቅት ውጊያ መካሄዱ ሲቪሎችን ለመጠበቅ የገቡትን ስምምነት አለማክበራቸውን ያሳያል።

የሱዳን ጦር ሰራዊት እና ፈጥኖ ደራሹ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) ባለፈው ሐሙስ በመርህ ደረጃ ተኩስ ለማቆም ስምምነት ካደረጉ ወዲህ፣ ውጊያው በካርቱም እና አካባቢው፣ እንዲሁም በዳርፉር ክልል መካሄዱ እንደቀጠለ ቢሆንም ቅዳሜ ጠዋት የነበረው ውጊያ ግን ካለፉት ሁለት ቀናት የባሰ እንደነበር እና አርኤስኤፍ የሚያንቀሳቅሷቸው ታንኮች በጉልህ ይሰሙ እንደነበር የ28 አመት እድሜ ያላት የከተማዋ ነዋሪ ሀኒ አህመድ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፃለች።

ከአንድ ወር በፊት ውጊያው ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲገደሉ፣ ከ200 ሺህ በላይ ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተሰደዋል፣ 700ሺህ የሚሆኑ ደግሞ በሀገር ውስጥ በመፈናቀላቸው በአካባቢው ባሉ የቀጠናው ሀገሮችም ያለመረጋጋት እንዳይፈጥር ስጋት ደቅኗል።

በጅዳ የቀጠለው ውይይት አሁን ያለው ስምምነት እንዴት መከበር እንደሚችል በመወያየት የሚጀመር ሲሆን በቀጣይ በሲቪሎች የሚመራ መንግስት መመስረት የሚያስችል መንገድ የሚከፍት ዘላቂነት ያለው የተኩስ ማቆም ስምምነት መድረስ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩ ባለስልጣናት ገልፀዋል።

ሳዑዲ አረቢያ የሱዳን መሪ የሆኑትን የጦር ኃይሉን አዛዥ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በጂዳ በሚካሄደው የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የጋበዘቻቸው መሆኑን አንድ የሳዑዲ ባለስልጣን የገለፁ ቢሆንም፣ ቡርሃን በደህነት ስጋት ምክንያት ከሱዳን መውጣት ላይችሉ እንደሚችሉ ሌሎች ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።

በየመን ሳዑዲ-መር የሆነው ጥምረት ከሁቲ ኃይሎች ጋር የሚያካሂደውን ውጊያ ለማገዝ የሱዳን ጦር ሰራዊት እና አር ኤስ ኤፍ ኃይሎች ወታደሮቻቸውን በመላካቸው፣ ሳዑዲ አረቢያ ከሁለቱም የሱዳን መሪዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት።

XS
SM
MD
LG