በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የአፍሪካ ኅብረት ቡድን 20ን እንዲቀላቀል እደግፋለሁ” ሾልዝ


የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ
የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ

የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ የአፍሪካ ኅብረት ቡድን 20 የተባለውንና በኢኮኖሚ የበለጸጉ አገሮችን ስብስብ መቀላቀሉን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

አፍሪካን በመጉብኘት ላይ ያሉት ሾልዝ እንዳሉት አቋማቸው ለአህጉሪቱ፣ በውስጡ ላሉት አገሮችና እያደገ ለመጣው የአህጉሪቱ ህዝብ ካላቸው ክብር የመነጨ ነው።

ሾልዝ ይህን ያስታወቁት ትናንት በአፍሪካ ጉዟቸው የመጀመሪያ በሆነችው ኢትዮጵያ የሚገኘውን የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት በጎበኙበት ወቅት ነው

በአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ጀርመን የበኩሏን ማድረግ እንደምትሻም ሾልዝ አስታውቀዋል።

ሾልዝ የአራት ቀናት የምሥራቅ አፍሪካ ጉዟቸውን በመቀጠል ዛሬ ኬንያ መዲና ናይሮቢ ገብተው ከፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተገናኝተዋል።

ሁለቱ መሪዎች የኢኮኖሚ ግንኙነትን በተመለከተ እንዲሁም በአህጉሪቱ እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG