በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂቡቲ ስደተኞችን ወደየአገራቸው መልሳ ልትልክ ነው


ፎቶ ፋይል፦አምቡሊ፣ ጂቡቲ እአአ ሚያዚያ 23/2017
ፎቶ ፋይል፦አምቡሊ፣ ጂቡቲ እአአ ሚያዚያ 23/2017

ጂቡቲ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያለቻቸውን ሦስት ሺሕ የሚደርሱ ስደተኞችን መያዟንና ወደ የመጡባቸው ሀገራት መልሳ እንደምትልካቸው ትላንት እሑድ አስታወቀች፡፡

የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳይድ ሓሳን፣ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ቀርበው በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ቀንዷ አገር ከአካባቢው በሚመጡ ስደተኞች ተጥለቅልቃለች፤ ብለዋል፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ፣ 222ሺሕ ስደተኞች ወደ አገሪቱ በሕገ ወጥ መንገድ መግባታቸውን ሚኒስትሩ አውስተዋል፡፡

አንድ ሚሊዮን የሚኾን የሕዝብ ብዛት ያላት ጂቡቲ፣ ግጭትንና ረኀብን ሽሽት ከቀጣናው ሀገራት ለሚሰደዱ ፍልሰተኞች መተላለፊያ ነች፡፡

ትላንት እሑድ የተያዙትና ሦስት ሺሕ የሚደርሱት ስደተኞች፣ በመኪና ተጭነው ወደየመጡባቸው ሀገራት ተመልሰው እንደሚላኩ ሚኒስትሩ ገልጸው፣ የሕዝባቸውን ደኅንነት ለመጠበቅ አሠሣው በመላዋ ጅቡቲ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG