በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ፣ የደቡብ ኮሪያ መሪ በአሜሪካ ያደረጉትን ጉዞ ተቸች


ፋይል - የደቡብ ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት፣ ኪም ዮ ጆንግ
ፋይል - የደቡብ ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት፣ ኪም ዮ ጆንግ

የሰሜን ኮሪያ መንግስት ሚዲያ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ኢዩን ወደ አሜሪካ ያደረጉትን ጉዞ በድጋሚ ተችቷል።

ሰሜን ኮሪያ ቅዳሜ እለት ይፋ ባደረገችው መግለጫ፣ የሀገሪቱ ኮሚኒስት ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት እና የመሪው ኪም ጆንግ ኡን እህት የሆኑት ኪም ዮ ጆንግ፣ የደቡብ ኮሪያው መሪ ዩን ሶክ ኢዩን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በመገናኘታቸው "ከዳተኛ አሻንጉሊት" ሲሉ ጠርተዋቸዋል።


ምንም አንኳን መግለጫው በፕሬዝዳንት ባይደን ላይ የተዘነዘሩ ዘለፋዎችን ባያካትትም፣ ዩናይትድ ስቴትስን ግን "የክፋት ግዛት" ሲል ጠቅሷታል። ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ እንደአዲስ ያደሷቸውን የደህንነት እቅዶች እና የኒውክሌር ዝግጅነቶች በመጥቀስም፣ ሁለቱ ሀገራት "ለሚያደርጉት አደገኛ ድርጊት ዋጋ ይከፍላሉ" ብሏል። በምላሹም ሀገራቸው ወታደራዊ ኃይላቸውን የሚያሳዩ ትርዒቶችን እንደምታካሂድም የደቡብ ኮሪያው መሪ እህት ተናግረዋል።

ባይደን ከደቡብ ኮሪያው መሪ ጋር በዋሽንግተን ያካሄዱት ስብሰባ የተካሄደው ሰሜን ኮሪያ የጦር አቅሟን ለማሳየት የምታደርጋቸው ትዕይንቶች እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ በጋራ የሚያካሂዷቸው ወታደራዊ ልምምዶች እየጨመሩ እና በኮሪያ አካባቢ ውጥረቱ እያየለ በመጣበት ወቅት ነው።

XS
SM
MD
LG