በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፖላንድ የሩሲያ ኤምባሲ ትምህርቤት በቁጥጥር ስር ማዋሏን ተከትሎ ሩሲያ ጠንካራ እርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች


በፖላንድ፣ ዋርሶ የሚገኘውን የሩሲያ ኤምባሲ ትምህርት ቤት ሰራተኞች ህንፃውን ለቀው ለመውጣት እቃቸውን ወደጭነት መኪና ሲያስገቡ
በፖላንድ፣ ዋርሶ የሚገኘውን የሩሲያ ኤምባሲ ትምህርት ቤት ሰራተኞች ህንፃውን ለቀው ለመውጣት እቃቸውን ወደጭነት መኪና ሲያስገቡ

ሩሲያ፣ በፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶ የሚገኘው ኤምባሲዋ ንብረት የሆነውን ትምህርት ቤት በህወገወጥ መንገድ መያዟ፣ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ ሀገራት የገቡትን የቪየና ስምምነት በግልፅ የጣሰ ነው ስትል፣ ለድርጊቱ ጠንከር ያለ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።


ቲቪፒ የተሰኘ የፖላንድ መንግስት ቴሌቭዥን ጣቢያ ባስተላለፈው ዘገባ፣ ቅዳሜ ጠዋት ፓሊስ ዋርሶ ከሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ትምህርት ቤት ውጪ ቆሞ አሳይቷል። ስለሁኔታው የተጠየቁት የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ለሮይተርስ በሰጡት ምላሽ፣ የኤምባሲው ትምህርት ቤት የሚገኝበት ህንፃ ንብረትነቱ የፖላንድ መንግስት ነው ብሏል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ የፖላንድ ባለስልጣናት ወደ ኤምባሲው ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ የገቡት ቦታውን ለመቆጣጠር ነው ያለ ሲሆን ድርጊቱ "እ.አ.አ በ1961 በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ዙሪያ የተደረሰውን የቪየና ስምምነት እና በፖላንድ የሚገኘውን የሩሲያ ንብረት የጣሰ ነው" ሲል አስታውቋል።


"ከዘመናዊ የሀገራት ግንኙነት ማዕቀፍ ውጪ የሆነው ይህ አይነቱ የዋርሶ እብሪተኛ እርምጃ፣ በፖላንድ ባለስልጣናት እና ፖላንድ በሩሲያ ባላት ፍላጎት ላይ ከባድ ምላሽ እና መዘዝ ማስከተሉ አይቀርም" ሲልም መግለጫው አስጠንቅቋል።

ሩሲያ የመቃወም መብት አላት ያሉት የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሉካሳ ያሲና በበኩላቸው፣ ፖላንድ ድርጊቱን የፈፀመችው በህግ አግባብ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።


ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከአካሄደች በኃላ ብዙም ሳይቆይ እ.አ.አ በመጋቢት 2022 ዓ.ም፣ ፖላንድ ለሞስኮ የስለላ ድርጅት ይሰራሉ ያለቻቸውን 45 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከሀገሯ እንደምታባርር አስታውቃ ነበር።

XS
SM
MD
LG