በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ የቅርብ ጊዜ የሚሳኤል ጥቃት የጦር ስልቷን ልትቀይር እንደምትችል አመላከተ


ሴቫስቶፖል፤ ክሬሚያ
ሴቫስቶፖል፤ ክሬሚያ

ዛሬ ቅዳሜ በክሬሚያ ሴቫስቶፖል ወደብ ላይ ነዳጅ በጫነች ታንክ ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል። የአካባቢው ሃገረ ገዥ ሚካኼል ራዝሔቭ፤ የተገኙ ፍንጮች አደጋው የደረሰው በድሮን ጥቃት የተነሳ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሴቫስቶፖል የክሬሚያ ከፍተኛ ቦታ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2014 ወደ ሩሲያ የተቀላቀለች ስፍራ ነው። ሩሲያ ዩክሬን በሴቫስቶፖል በተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን አድርሳለች ስትል ወንጅላለች።

የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር ቅዳሜ ዕለት በትዊተር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፍተኛ የሆነ “ሩሲያ የረጅም ርቀት ጥቃቶችን እንደምትፈጽም ምልክት አለ” ሲል አስታውቋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አክሎም ሩሲያ በክረምቱ ወራት ስታደርግ እንደነበረው የዩክሬንን የሃይል አቅርቦት መሰረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን ‘በቅርቡ ለዩክሬን የተሰጡ ወታደራዊ አቅርቦቶችን ለመጥለፍ እየሞከረች ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አለ" ሲል አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG