በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በሶሪያ ሆምስ ግዛት የአየር ድብደባ አደረሰች


ሶሪያ፤ ሆምስ
ሶሪያ፤ ሆምስ

የሶሪያ መንግስት የዜና ወኪል ሳና በሶሪያ ሶስት ንፁሀን ዜጎች መቁሰላቸውን፣ ነዳጅ ማደያ በእሳት መቃጠሉን፣በርካታ ነዳጅ ጫኚዎች እና የጭነት መኪናዎች መቃጠላቸውን ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

የሶሪያ መንግስት ደጋፊ የሆነው ሻም የተሰኘ ኤፍ ኤም፤ የእስራኤል ሚሳኤሎች ሆምስ በተሰኘው የሃገሪቱ ክፍል በአየር ድብደባ ማድረጋቸውን ገልጾ፤ በምላሹ ሚሳኤሎች ተተኩሰው የተወሰኑት መውደቃቸውን ዘግቧል።

መቀመጫውን ብሪታንያ ያደረገው የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ ቡድን የእስራኤል ሚሳኤሎች ሆምስ በተሰኘው የሶሪያ ገጠራማ ክፍል የሚገኘውን የሂዝቦላ አማጺ ቡድን የጥይት ማከማቻ አውድመዋል ብሏል።

ታዛቢዎች እስራኤል በአንድ ወር ውስጥ ቦታውን ለሁለተኛ ጊዜ ማጥቃቷን አስታውቀዋል። እ.ኤ.አ በሚያዚያ 2 እስራኤል ባደረሰችው የአየር ድብደባ በሆምስ በርካታ ቦታዎችን መምታቷን እና አምስት ወታደሮችን ማቁሰሏን የሃገሪቱ የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG