በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱርኩ ፕሬዘዳንት ኤዶጋን የምርጫ ቅስቀሳቸውን ለሶስተኛ ጊዜ ሰረዙ


የቱርክ ፕሬዘዳንት ኤርዶጋን
የቱርክ ፕሬዘዳንት ኤርዶጋን

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬጂብ ጣይብ ኤርዶጋን በህመም ምክንያት ለሶስተኛ ጊዜ የምርጫ ቅስቀሳቸውን ሰረዙ። የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ፕሬዘዳንቱ በአንጀት ኢንፌክሽን መታመማቸውን አስታውቀዋል።

ቱርክን ለሁለት አስርት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከዚያም በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኤርዶጋን በጎርጎሮሳዊያኑ ግንቦት 14 በሃገሪቱ ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለሦስተኛ ዙር ይወዳደራሉ። በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል አዳና ከተማ በተሰናዳ ድልድይ ምርቃት ላይ እና የፖለቲካ ስብሰባ ላይ መገኘት የነበረባቸው ቢሆንም መርሃግብሩ ተቀይሮ የመክፈቻ ስርዓቱ በቪዲዮ እንዲተላለፍ ተደርጎ ነበር።

የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ፕሬዘዳንት ኤርዶጋን አርብ ዕለት ከዩክሬን-ሩሲያ የእህል እና የማዳበሪያ ስምምነትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል። በመጪው የአውሮፓዊያኑ ግንቦት 18 የሚጠናቀቀው የስምምነቱ ማሻሻያ፣ መስፋፋትና ማራዘሚያ እንዴት ማረጋገጥ እንደሚቻል መወያየታቸውን ተናግረዋል።

ኤርዶጋን ሃሙስ ዕለት ከረዥም ጊዜ በኋላ የኑክሌር ሃይል ማብላያ ሲያስመርቁ በቴሌቪዥን መስኮት የታዩ ሲሆን፤ በማግስቱ አርብ ዕለትም ከጠረጴዛ ጀርባ ሆነው ለ10ደቂቃዎች ንግግር ሲያደርጉ በቪዲዮ ታይተዋል።

XS
SM
MD
LG