በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የልዩ ተልዕኮ ኃይሎች የዩኤስ አምባሲ ባልደረቦችን ከካርቱም አስወጡ


የልዩ ተልዕኮ ኃይሎች የዩኤስ አምባሲ ባልደረቦችን ከካርቱም አስወጡ
የልዩ ተልዕኮ ኃይሎች የዩኤስ አምባሲ ባልደረቦችን ከካርቱም አስወጡ


የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ የጦር ተልዕኮ ኃይሎች የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን እና ቤተሰቦቻቸውን ካርቱም ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እሁድ ማለዳ በተሳካ ሁኔታ ማስወጣታቸው ተገለጸ። ተልዕኮው ከአንድ ሰአት ባነሰ ጊዜ እንደተጠናቀቀ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ሰራተኞቿን ከካርቱም እንደምታስወጣ በዛሬው ዕለት አስታውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቅዳሜ ማለዳ ላይ በሰጡት መግለጫ የካርቱም ኤምባሲ ስራዎች በጊዚያዊነት እንደተቋረጡ ይፋ አድርገዋል።

ብሊንከን ኤምባሲውን እንዲዘጋ ያዘዙት በሱዳን ጦር ኃይሎች እና በፈጣን ደጋፊ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት የፈጠረውን አደገኛ እና እየተስፋፋ የመጣ ስጋት በመመልከት እንደሆነ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው፣ ቅዳሜ አመሻሹን በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካዊያኑን የማስወጣቱ ሂደት መጠናቀቁን አስታውቀው ፣ተልዕኮውን የፈጸሙትን የአሜሪካ ወታደሮችን አመስግነዋል።

" የኤምባሲያችን ሰራተኞች ተግባራቸውን በድፍረት እና በሙያዊ ብቃት በመወጣት አሜሪካ ከሱዳን ህዝብ ጋር ያላትን ወዳጅነት እና ግንኙነት ባሳየው ያልተለመደው ቁርጠኝነትታቸው ኩራት ተሰምቶኛል " ሲሉ ባይደን ተናግረዋል።

ባይደን ለተልዕኮው መሳካት ወሳኝ ሚና እንደተጫወቱ ለጠቀሷቸው ለጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ወደ 70 የሚጠጉ አሜሪካውያን ሱዳን ውስጥ ከሚገኘው ኤምባሲው ወደ ኢትዮጵያ በአውሮፕላን መወሰዳቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል ። በእንቅስቃሴው ወቅት በኤምባሲ ውስጥ የነበሩት የሌሎች ኤምባሲዎች ዲፕሎማሲያዊ ባልደረቦችም በአየር የመጓጓዙ ሂደት ውስጥ መካተታቸውን አንድ ባለስልጣን ተናግረዋል።

ባይደን ትዕዛዙን የሰጡት፣ ጦርነቱ እንደማይበርድ ቅዳሜ ዕለት ከብሄራዊ ደህንነት አማካሪዎች ከቀረበላቸው ግምገማ በኃላ ነበር።

XS
SM
MD
LG