በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሰመጠ መርከብ ከ80 ዓመታት በኋላ ተገኘ


ሳይለንትውድ የተሰኘው የአውስትራሊያ ፋውንዴሽን እ.አ.አ በሚያዚያ 22፣ 2023 ዓ.ም ይፋ ያደረገው ፎቶ 'ሞንቴቪዴዮ ማሩ' የተሰኘችው እና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት የነበረች የጃፓን ህዝብ ማመላለሻ መርከብን ምስል ያሳያል
ሳይለንትውድ የተሰኘው የአውስትራሊያ ፋውንዴሽን እ.አ.አ በሚያዚያ 22፣ 2023 ዓ.ም ይፋ ያደረገው ፎቶ 'ሞንቴቪዴዮ ማሩ' የተሰኘችው እና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት የነበረች የጃፓን ህዝብ ማመላለሻ መርከብን ምስል ያሳያል

በዓለም ላይ ካሉት አስከፊ ዓለም አቀፍ የባህር አደጋዎች አንዱ የሆነው እንቆቅልሽ በፊሊፒንስ የባህር ዳርቻ ላይ ተፈቷል። የጃፓን የህዝብ ማመላለሻ የሆነው እና በአሜሪካ ባህር ሰርጓጅ መርከብ የሰጠመችው 'ሞንቴቪዴዮ ማሩ' የተሰኘች መርከብ ስብርባሪ ከ80 ዓመታት በኃላ ተገኝቷል። በዚህ የመርከብ አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያንን ጨምሮ ወደ 1ሺህ የሚጠጉ የጦር እስረኞች ተገድለዋል።


ሞንቴቪዴዮ ማሩ በወቅቱ ጃፓን እ.አ.አ በ1942 ዓ.ም ከፓፑዋ ኒው ጊኒ የያዘቻቸውን 850 የጦር እስረኞች እና 200 ሲቪሎችን ይዛ እየተጓዘች የነበረች ሲሆን በውስጧ የያዘቻቸውን ሰዎች ማንነት ባላወቀው የአሜሪካ ሰርጓጅ መርከብ እንድትገልበጥ ተደርጋለች።

መርከቧ ከተገለበጠች በኃላ ግን የደረሰችበት መጥፋቱ እስካሁን እንቆቅልሽ ሆኖ የቆየ ሲሆን፣ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የመርከቧ ስብርባሪ በፊሊፒንስ ዳርቻ፣ በደቡብ ቻይና ባህር ውስጥ ተገኝቷል። መርከቧን የማግኘቱ ተልዕኮ የተፈፀመው የአውስታሪያ መከላከያ ሚኒስትር፣ ሳይለትውድ የተሰኘ የአውስታራሊያ የባህር ውስጥ ስነ-ቅርስ ምርምር ፋውንዴሽን እና የኔዘርላንድ ጥልቅ የባህር ጥናት ባለሙያዎች ባደረጉት የጋራ ጥረት ነው።

በወቅቱ የደረሰው አደጋ ከ12 በላይ ሀገራትን የነካ ሲሆን ከአውስትራሊያ እና ከጃፓን በተጨማሪ፣ የዴንማርክ፣ የኒውዚላንድ፣ እና የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችም ተጎጂዎች ነበሩ።

XS
SM
MD
LG