በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ግጭት ምክንያት አንዳንድ የመዲናዋ ነዋሪዎች እየሸሹ ነው


ከካርቱም ሸሽተው ለመሰደድ የሚሞክሩ ሰዎች በአዎቶቢስ መሳፈሪያ ጣቢያ ተሰብስበው ይታያሉ
ከካርቱም ሸሽተው ለመሰደድ የሚሞክሩ ሰዎች በአዎቶቢስ መሳፈሪያ ጣቢያ ተሰብስበው ይታያሉ

በሱዳን ሊደረስ የተሞከረው የተኩስ ማቆም ስምምነት በተደጋጋሚ መክሸፉን ተከትሎ አልፎ አልፎ የተኩስ ድብደባ ድምፆች በቀጠሉባት ዋና ከተማ አጣብቂኝ ውስጥ የገቡት ነዋሪዎች አሁንም በየቤታቸው የተደበቁ ሲሆን ከከተማዋ ለመውጣት የቻሉ ደግሞ በመሸሽ ላይ ናቸው።

ከከተማዋ በስተደቡብ የሚገኘው የነጭ አባይ ግዛት ውስጥ ተማሪ የሆነው አናስ መሀመድ ጎረቤቱ በጥይት ሲመታ እና ጥይቶች በቤቱ ላይ እየበረሩ ሲያልፉ ማየቱ አካባቢውን ጥሎ ለመሄድ እንዳስገደደው ገልጿል።

"በዋና ከተማ አሁን ምንም አይነት አስተማማኝ ቦታ የለም" የሚለው መሀመድ "አሁንም በካርቱም ለሚቆዩት ምንም አይነት ጉዳይ እንዳይደርስባቸው ሰላም እና ደህንነት እንመኛለን" ብሏል።

በከተማው የመብራት መቆራረጥ እና የውሃ እና የምግብ አቅርቦት እየቀነሰ በመምጣቱ የተሻለ ደህንነት ያለው ቦታ እየፈለጉ ያሉት ነዋሪዎች የግጭቱ መንስዔ ምን እንደሆነ እና ሰላም መምጣት ስለሚችልበት ተስፋ ለማወቅም ይጓጓሉ።

ከነዋሪዎቹ በተጨማሪም፣ ከሌሎች ሀገራት ግጭት ሸሽተው የመጡ በካርቱም የሚኖሩ ስደተኞችም እንዲሁ ጥበቃ ሰላም እንዲወርድ እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ተማጽኖአቸውን እያሰሙ ነው።

XS
SM
MD
LG